2 ጢሞቴዎስ 4:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከቶም እውነትን ከመስማት ጆሮዎቻቸውን ይመልሳሉ፤ መንገድንም ስተው ወደ ተረት ፈቀቅ ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነትን ከመስማት ጆሯቸውን ይመልሳሉ፤ ወደ ተረትም ዘወር ይላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እውነትን መስማት ትተው ተረትን መስማት ይወዳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እውነትንም ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ፤ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እውነትንም ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ፥ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ። |
በዓይናቸው አይተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸውም አስተውለው፥ ተመልሰው እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፥ ጆሮአቸው ደንቁሮአል፥ ዓይናቸውም ተጨፍኖአል፤
ራሳቸውንም በተረት፥ መጨረሻም በሌለው የትውልዶች ታሪክ እንዳይጠመዱ እንድታዝ ለመንሁህ፤ ሆኖም ግን እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ከንቱ ምርምር ያመጣሉ እንጂ በእምነት የሚገኝውን የእግዚአብሔርን መጋቢነት አይጠቅሙም።
ነገር ግን ከረከሰው ከዚህ ዓለም አፈ ታሪክና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አለማምድ።
ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይልና መምጣቱም በነገርናችሁ ጊዜ፥ ራሳችን ግርማውን በዐይናችን አይተን የምንመሰክር እንጂ፥ በሰው ብልጠት የታቀደውን ተረት ተከትለን አይደለም።