2 ተሰሎንቄ 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናንተ ጋር በነበርሁ ጊዜ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችሁ እንደ ነበረ አታስታውሱምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእናንተ ጋራ በነበርሁበት ጊዜ፣ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችሁ እንደ ነበር ትዝ አይላችሁምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ ይህን ነገር ነግሬአችሁ እንደ ነበረ አታስታውሱምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገና ከእናንተ ጋር ሳለሁ ይህን እንዳልኋችሁ ትዝ አይላችሁምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገና ከእናንተ ጋር ሳለሁ፥ ይህን እንዳልኋችሁ ትዝ አይላችሁምን? |
ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ እኔ እንደ ነገርኋችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። ከእናንተም ጋር ስለ ነበርሁ በመጀመሪያ ይህን አልነገርኋችሁም።
ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ መሶልሶል፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜ እንደ ነገርኋችሁ፥ አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።