Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ተሰሎንቄ 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ገና ከእናንተ ጋር ሳለሁ ይህን እንዳልኋችሁ ትዝ አይላችሁምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከእናንተ ጋራ በነበርሁበት ጊዜ፣ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችሁ እንደ ነበር ትዝ አይላችሁምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ከእናንተ ጋር በነበርሁ ጊዜ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችሁ እንደ ነበረ አታስታውሱምን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ ይህን ነገር ነግሬአችሁ እንደ ነበረ አታስታውሱምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ገና ከእናንተ ጋር ሳለሁ፥ ይህን እንዳልኋችሁ ትዝ አይላችሁምን?

Ver Capítulo Copiar




2 ተሰሎንቄ 2:5
11 Referencias Cruzadas  

ከመውጣቴም በኋላ እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ።


ደግሞ ከእናንተ ጋር ሳለን “ሊሠራ የማይወድ አይብላ፤” ብለን አዘናችሁ ነበርና።


ወደ መንግሥቱ ወደ ክብሩም ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እየመከርንና እያጸናን እየመሰከርንላችሁም፥ አባት ለልጆቹ እንደሚሆን ለእያንዳንዳችሁ እንደ ሆንን ታውቃላችሁና።


አስ​ቀ​ድሜ እንደ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት አያ​ይም።


ስለ​ዚ​ህም ትጉ፤ እኔ ሁላ​ች​ሁ​ንም ሳስ​ተ​ምር ሦስት ዓመት ሙሉ ሌትም ቀንም እን​ባዬ እን​ዳ​ል​ተ​ገታ ዐስቡ።


ነገር ግን ጊዜው ሲደ​ርስ እኔ እንደ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ። አስ​ቀ​ድሜ ግን ይህን አል​ነ​ገ​ር​ክ​ኋ​ች​ሁም ነበር፤ ከእ​ና​ንተ ጋር ነበ​ር​ሁና።


ልባችሁስ ደንዝዞአልን? ዐይን ሳላችሁ አታዩምን? ጆሮስ ሳላችሁ አትሰሙምን? ትዝስ አይላችሁምን?


ለአምስቱ ሺህ አምስቱ እንጀራ፥ ስንት መሶብም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?


በእውነት ከእናንተ ጋር ሳለን፥ መከራ እንቀበል ዘንድ እንዳለን አስቀድመን እንነግራችሁ ነበር፤ እንዲሁም ደግሞ ሆነ፤ ይህንም ታውቃላችሁ።


በገዛ ራሱ ጊዜም ይገለጥ ዘንድ የሚከለክለውን አሁን ታውቃላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios