አዳምንም ካስወጣው በኋላ፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና በሁሉም አቅጣጫ የምትውለበለብ ነበልባላዊ ሰይፍን በዔድን ገነት በስተ ምሥራቅ አስቀመጠ።
2 ተሰሎንቄ 1:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችንም ለኢየሱስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰማይ የሚገለጠውም በሚንበለበል እሳት ነው፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችን ለኢየሱስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይቀጣቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤ |
አዳምንም ካስወጣው በኋላ፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና በሁሉም አቅጣጫ የምትውለበለብ ነበልባላዊ ሰይፍን በዔድን ገነት በስተ ምሥራቅ አስቀመጠ።
ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
ያዕቆብን በልተውታልና፥ ውጠውታልምና፥ አጥፍተውታልምና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ መዓትህን አውርድ።
ከዚህ በኋላ በግራው ያሉትን ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ።
ስለዚህም “አባትህ ወዴት ነው?” አሉት። ኢየሱስ መልሶ “እኔንም ሆነ አባቴንም አታውቁም፤ እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ደግሞ ባወቃችሁ ነበር፤” አላቸው።
የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፤ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ።
እራሳችሁን የመታዘዝ ባርያዎች አድርጋችሁ ለምታቀርቡለት፥ ለምትታዘዙት ለእርሱ ሞትን ለሚያመጣው ለኃጢአት ወይም ጽድቅን ለሚያመጣው ለመታዘዝ ባርያዎች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን?
በእግዚአብሔር እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ክርክርና ማንኛውም የእብሪት እንቅፋት እናፈርሳለን፤ አእምሮን ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን፤
እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፥ እስከ ሰማይም ድረስ እሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፥ ጨለማም ደመናና ድቅድቅ ጨለማ ነበረ።
እናንተ በእሳቱ ምክንያት ፈርታችሁ፥ ወደ ተራራውም አልወጣችሁምና፤ በዚያን ጊዜ፥ እኔ የጌታን ቃል ልነግራችሁ፥ በጌታና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር። እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ ይህንኑ አረጋግጠውልናል።
እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ ያወቃችሁ፥ በመንፈስ የተቀደሳቹ፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ትታዘዙና በደሙም ትረጩ ዘንድ ለተመረጣችሁት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአል፤ በቅድሚያም በእኛ የሚጀመር ከሆነ፥ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?
ነገር ግን አሁን ያሉት ሰማያትና ምድር በዚሁ ቃል፥ እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ለእሳት ተጠብቀው ይቆያሉ።
እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች፥ እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ በዘለዓለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።
ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፤ ከዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ቀንና ሌሊት ይሰቃያሉ።
ነገር ግን የሚፈሩ፥ የማያምኑ፥ የሚረክሱ፥ ነፍሰ የሚያጠፉ፥ የሚሴሰኑ፥ አስማትን የሚያደርጉ፥ ጣዖትንም የሚያመልኩና የሚዋሹ ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”
በታላቅ ድምፅም እየጮኹ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ።