አቢሳንም ተከትለው የኢዮአብ ሰዎች ከሊታውያን፥ ፈሊታውያን፥ እንዲሁም ሌሎች ኀያላን ጦረኞች በሙሉ ወጡ፤ የቢክሪ ልጅ ሼባዕን ለማሳደድ ከኢየሩሳሌም ወጡ።
2 ሳሙኤል 20:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአብ በእስራኤል ሠራዊት ሁሉ ላይ አዛዥ ሆነ፤ የዮዳሄ ልጅ በናያ ደግሞ በከሊታውያንና በፈሊያታውያን ላይ አዛዥ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአብ በእስራኤል ሰራዊት ሁሉ ላይ የበላይ ሆነ፤ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ደግሞ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ አለቃ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብ የእስራኤል ሠራዊት አዛዥ ሲሆን፥ የዮዳሄ ልጅ በናያ የዳዊት ክብር ዘብ ኀላፊ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም በእስራኤል ሠራዊት ሁሉ ላይ አለቃ ነበረ፤ የዮዳሄም ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ አለቃ ነበረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም በእስራኤል ሠራዊት ሁሉ ላይ አለቃ ነበር፥ የዩዳሄም ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፥ |
አቢሳንም ተከትለው የኢዮአብ ሰዎች ከሊታውያን፥ ፈሊታውያን፥ እንዲሁም ሌሎች ኀያላን ጦረኞች በሙሉ ወጡ፤ የቢክሪ ልጅ ሼባዕን ለማሳደድ ከኢየሩሳሌም ወጡ።
የቃብጽኤል አገር ሰው የሆነው የዮዳሄ ልጅ በናያም ታላቅ ተግባር የፈፀመ ሌላው ጐበዝ ተዋጊ ነበረ፤ ሁለቱን በጣም የታወቁ የሞዓብን ሰዎችን ገድሎአል፤ እንዲሁም በረዶ በጣለበት ዕለት በጉድጓድ ውስጥ ገብቶ አንበሳ ገድሎአል፤
ነገር ግን በሰባተኛው ዓመት ካህኑ ዮዳሄ ለንጉሡ ክብር ዘቦችና ለቤተ መንግሥቱ ጠባቂዎች ሁሉ ኃላፊዎች ወደ ሆኑት የጦር መኰንኖች ሁሉ ልኮ ወደ ቤተ መቅደስ እንዲመጡ አስጠራቸው፤ በዚያም ሊያደርገው ያቀደውን ይስማሙበት ዘንድ በመሐላ እንዲያረጋግጡለት አደረገ፤ ከዚያም በኋላ የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን አሳያቸውና፥