Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 23:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የቃብጽኤል አገር ሰው የሆነው የዮዳሄ ልጅ በናያም ታላቅ ተግባር የፈፀመ ሌላው ጐበዝ ተዋጊ ነበረ፤ ሁለቱን በጣም የታወቁ የሞዓብን ሰዎችን ገድሎአል፤ እንዲሁም በረዶ በጣለበት ዕለት በጉድጓድ ውስጥ ገብቶ አንበሳ ገድሎአል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የቀብጽኤል አገር ሰው የሆነው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ታላቅ ጀብዱ የሠራ ሌላው ጐበዝ ተዋጊ ነበረ፤ እርሱም ሁለት በጣም የታወቁ የሞዓብ ሰዎችን ገደለ፤ እንዲሁም በረዶ በጣለበት ዕለት በጕድጓድ ውስጥ ገብቶ አንበሳ ገድሏል፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ሌላው ዝነኛ ወታደር የቃብጽኤል ተወላጅ የነበረው የዮዳሄ ልጅ በናያ ነበር፤ እርሱም ሁለት የታወቁ ሞአባውያን ወታደሮችን ከመግደሉም ሌላ ብዙ የጀግንነት ሥራ ፈጽሞአል፤ አንድ ጊዜ በምድር ላይ ዐመዳይ በወረደበት ቀን ወደ አንድ ዋሻ ወርዶ አንበሳ ገደለ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በቀ​በ​ስ​ሄል የነ​በ​ረው ታላቅ ሥራ ያደ​ረ​ገው የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ የሞ​ዓ​ባ​ዊ​ውን የአ​ር​ኤ​ልን ሁለት ልጆች ገደለ፤ በአ​መ​ዳ​ዩም ወራት ወርዶ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ አን​በሳ ገደለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በቀብጽኤል የነበረው ታላቅ ሥራ ያደረገው የጽኑዕ ሰው የዮዳሄ ልጅ በናያስ የሞዓባዊውን የቀብስኤልን ሁለት ልጆች ገደለ፥ በአመዳዩም ወራት ወርዶ በጕድጓድ ውስጥ አንበሳ ገደለ።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 23:20
19 Referencias Cruzadas  

ሳኦልና ዮናታን፥ የተዋደዱና የተስማሙ፤ በሕይወትም ሆነ በሞት ያልተለያዩ፤ ከንስርም ይልቅ የፈጠኑ፥ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።


ኢዮአብ በእስራኤል ሠራዊት ሁሉ ላይ አዛዥ ሆነ፤ የዮዳሄ ልጅ በናያ ደግሞ በከሊታውያንና በፈሊያታውያን ላይ አዛዥ ሆነ።


እርሱ ከሠላሳው ይልቅ እጅግ ዝነኛ ስለ ነበር፤ አለቃቸው ሆኖ ነበር፥ ነገር ግን ወደ ሦስቱ ደረጃ አልደረሰም።


አንድ ማራኪ ግብፃዊንም ገድሎአል፤ ግብፃዊው በእጁ ጦር ይዞ፥ በናያ ግን ሊገጥመው በትር ይዞ ነበር ወደ እርሱ የሄደው፤ ከግብፃዊውም እጅ የገዛ ጦሩን በመንጠቅ ገደለው።


የዮዳሄ ልጅ በናያ ያደረገው ይህ ነው፥ ስሙም እንደ ሦስቱ ኃያላን ተጠርቶ ነበር።


የዮዳሔ ልጅ በናያ የከሪታውያንና የፈሊታውያን አለቃ ሲሆን፥ የዳዊት ወንዶች ልጆች ደግሞ አማካሪዎች ነበሩ።


ነገር ግን እኔን ባርያህን፥ ካህኑንም ሳዶቅን፥ የዮዳሄንም ልጅ በናያስን፥ ባርያህንም ሰሎሞንን አልጠራም።


ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን የዮዳሄም ልጅ በናያስ ከሊታውያንና ፈሊታውያንም ወረዱ፥ ሰሎሞንንም በንጉሡ በዳዊት በቅሎ ላይ አስቀምጠው ወደ ግዮን አመጡት።


ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅና የዮዳሄ ልጅ በናያ፥ ነቢዩም ናታን፥ ሺምዒና ሬዒ፥ የዳዊትም ተዋጊዎች ከአዶንያስ ጋር አልነበሩም።


ከዚህም በኋላ ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ሺምዒን እንዲገድል ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ ሺምዒን ገደለው፤ በዚህም ዓይነት መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ የጸና ሆነ።


ዳዊትም በምድረ በዳ ውስጥ ባለችው በአምባይቱ ሳለ ከጋድ ወገን የሆኑ እነዚህ በጋሻና በጦር ስልታቸው የተካኑ፥ ጽኑዓን ኃያላን፥ ተዋጊዎች፥ ወደ እርሱ መጡ፤ ፊታቸውም እንደ አንበሳ ፊት ነበረ፥ በተራራም ላይ እንደሚዘልል ሚዳቋ ፈጣኖች ነበሩ።


የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፤ የዳዊትም ልጆች በንጉሡ አጠገብ አለቆች ነበሩ።


የዚያን ጊዜ የኤዶም አለቆች ደነገጡ፤ የሞዓብ መሪዎች መንቀጥቀጥ ያዛቸው፤ በከነዓን የሚኖሩ ሁሉ ቀለጡ።


በደቡብም በኩል በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉት የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ቀብሴኤል፥ ዔደር፥ ያጉር፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos