La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 19:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህም ሕዝቡ በሙሉ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ንጉሡም ተሻገረ። ንጉሡ ባርዚላይን ስሞ መረቀው፤ ባርዚላይም ወደ ቤቱ ተመለሰ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሡ ወደ ጌልገላ ሲሄድ፣ ከመዓም ዐብሮት ሄደ። የይሁዳ ሰራዊት በሙሉ እንዲሁም ግማሹ የእስራኤል ሰራዊት ንጉሡን አጅበው አሻገሩት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ንጉሥ ዳዊት በይሁዳ ሕዝብ ሁሉና በእስራኤል ሕዝብ እኩሌታ ታጅቦ ወንዙን ከተሻገረ በኋላ ወደ ጌልጌላ አቀና፤ ኪምሀምም አብሮት ተሻገረ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉ​ሡም ወደ ጌል​ገላ ተሻ​ገረ፤ ከመ​ዓ​ምም ከእ​ርሱ ጋር ተሻ​ገረ፤ የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ሁሉ፥ ደግ​ሞም የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ እኩ​ሌታ ከን​ጉሡ ጋር ተሻ​ገሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሡም ወደ ጌልገላ ተሻገረ፥ ከመዓምም ከእርሱ ጋር ሄደ፥ የይሁዳም ሕዝብ ሁሉ ደግሞም የእስራኤል ሕዝብ እኩሌታ ንጉሡን አሻገረው።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 19:40
6 Referencias Cruzadas  

በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፥ ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ፥ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።


በመላው የእስራኤል ነገዶችም፥ ሕዝቡ እንዲህ እያለ እርስ በርሱ ይከራከር ነበር፤ “ንጉሡ ከጠላቶቻችን እጅ አውጥቶናል፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ የታደገን እርሱ ነው፤ አሁን ግን በአቤሴሎም ምክንያት ከአገር ሸሽቶ ሄዶአል፤


አገልጋይህ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ከንጉሡ ጋር ጥቂት መንገድ ይሄዳል፤ ነገር ግን ንጉሡ በዚህ ሁኔታ ወሮታ የሚመልስልኝ ለምንድን ነው?


ስለዚህ ንጉሡ ተነሥቶ በበሩ አጠገብ ተቀመጠ፤ ለሕዝቡም፥ “እነሆ ንጉሡ በበሩ አጠገብ ተቀምጦአል” ተብሎ በተነገረ ጊዜ ሕዝቡ በሙሉ ወደ ንጉሡ መጣ። በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን በሙሉ ወደየቤታቸው ሸሽተው ነበር።


ከፊቱ ይሄዱ የነበሩትና ይከተሉት የነበሩት ሕዝብ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።