La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 19:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አማሳይንም፥ ‘አንተስ የዐጥንቴ ፍላጭ፥ የሥጋዬ ቁራጭ አይደለህምን? ከአሁን ጀምሮ እስከ ሕይወትህ ፍጻሜ በኢዮአብ ምትክ የሠራዊቴ አዛዥ ባላደርግህ፥ እግዚአብሔር ክፉ ያድርግብኝ፥ ከዚህ የባሰም ያምጣብኝ’ ብላችሁ ንገሩት።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም የይሁዳን ሰዎች ልብ ሁሉ እንደ አንድ ሰው ልብ አድርጎ ማረከው፤ እነርሱም “አንተም ሰዎችህም ሁሉ ተመለሱ” ብለው ወደ ንጉሡ ላኩበት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የዳዊት አነጋገር የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ለእርሱ ታማኞች እንዲሆኑ አደረጋቸው፤ ስለዚህም ከመኳንንቱ ሁሉ ጋር ተመልሶ እንዲመጣ ላኩበት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የይ​ሁ​ዳ​ንም ሰዎች ሁሉ ልብ እንደ አንድ ሰው ልብ አድ​ርጎ አዘ​ነ​በለ፤ ወደ ንጉ​ሡም፥ “አን​ተና ብላ​ቴ​ኖ​ችህ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም ሁሉ ተመ​ለሱ” ብለው ላኩ​በት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የይሁዳንም ሰዎች ሁሉ ልብ እንደ አንድ ሰው ልብ አድርጎ አዘነበለ፥ ወደ ንጉሡም ልከው፦ አንተ ከባሪያዎችህ ሁሉ ጋር ተመለስ አሉት።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 19:14
8 Referencias Cruzadas  

አቤሴሎምም በኢዮአብ ምትክ አማሳይን በሠራዊቱ ላይ ሾመ፤ አማሳይ የእስማኤላዊው የዮቴር ልጅ ነበረ፤ ዮቴርም የኢዮአብን እናት፥ የጽሩያን እኅት፥ የናዖስን ልጅ አቢግያንሰ አግብቶ ነበር።


ከዚያም ንጉሡ አማሳይን፥ “የይሁዳ ሰዎች ሁሉ በሦስት ቀን ውስጥ፥ ወደ እኔ እንዲመጡ ጥራልኝ፤ አንተ ራስህም እንድትገኝ” አለው።


ከሕዝቤ ጥቃት አዳንከኝ፤ የመንግሥታትም ራስ አደረግኸኝ፤ የማላውቀው ሕዝብ ተገዛልኝ፤


ጌታ ለዳዊት በመሐላ የሰጠውን ተስፋ ከፍጻሜ ሳላደርስ ብቀር እግዚአብሔር በአበኔር ላይ ይፍረድ፤ ከዚያ የባሰም ያምጣበት፤


የእስራኤል ነገዶች በሙሉ ወደ ኬብሮን ወደ ዳዊት መጥተው እንዲህ አሉ፤ “እነሆ እኛ የዐጥንትህ ፍላጭ፥ የሥጋህ ቁራጭ ነን፤


ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፤ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደሆነ ማንም አልተናገረም።


ከዚያም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እንዲሁም በገለዓድ ምድር የሚገኙ እስራኤላውያን ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወጡ፤ በምጽጳም በጌታ ፊት ተሰበሰቡ።