ለባርያህ ካሳየኸው ከጽኑ ፍቅርና ከታማኝነትህ ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፥ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበር፥ አሁን ግን ለሁለት ወገን የተከፈልኩ ሆንሁ።
2 ሳሙኤል 17:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤሴሎም ከመላው የእስራኤል ሰዎች ጋር ዮርዳኖስን ሲሻገር፥ ዳዊት ግን ማሕናይም ደርሶ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቤሴሎም ከመላው የእስራኤል ሰዎች ጋራ ዮርዳኖስን ሲሻገር፣ ዳዊት ግን መሃናይም ደርሶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤሴሎምና እስራኤላውያን ሁሉ የዮርዳኖስን ወንዝ በተሻገሩ ጊዜ ዳዊት ማሕናይም ተብላ ወደምትጠራው ትንሽ ከተማ ደርሶ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወደ ምናሄም መጣ፤ አቤሴሎምም፥ ከእርሱ ጋር የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ዮርዳኖስን ተሻገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወደ መሃናይም መጣ፥ አቤሴሎምም ከእርሱም ጋር የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ዮርዳኖስን ተሻገሩ። |
ለባርያህ ካሳየኸው ከጽኑ ፍቅርና ከታማኝነትህ ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፥ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበር፥ አሁን ግን ለሁለት ወገን የተከፈልኩ ሆንሁ።