La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 10:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሀዳድዔዜር ሥር የነበሩት ነገሥታት ሁሉ በእስራኤል መሸነፋቸውን ባዩ ጊዜ ከእስራኤላውያን ጋር ሰላም መሠረቱ፤ ተገዙላቸውም። ከዚያም በኋላ ሶርያውያን ዳግመኛ ዐሞናውያንን ለመርዳት ፈሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በአድርአዛር ሥር የነበሩት ነገሥታት ሁሉ በእስራኤል መሸነፋቸውን ባዩ ጊዜ ከእስራኤላውያን ጋራ ሰላም መሠረቱ፤ ተገዙላቸውም። ስለዚህም ሶርያውያን ከዚያ በኋላ አሞናውያንን መርዳት ፈሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሀዳድዔዜር ሥልጣን ሥር የነበሩት ነገሥታት በእስራኤላውያን ድል መመታታቸውን በተገነዘቡ ጊዜ ከእነርሱ ጋር የሰላም ስምምነት አድርገው የእስራኤላውያን ተገዢዎች ሆኑ፤ ከዚያም በኋላ ሶርያውያን ዳግመኛ ዐሞናውያንን ለመርዳት ፈሩ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለአ​ድ​ር​አ​ዛ​ርም የሚ​ገ​ብሩ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እንደ ተሸ​ነፉ ባዩ ጊዜ ለእ​ስ​ራ​ኤል ተገዙ፤ ገበ​ሩ​ላ​ቸ​ውም። ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ከዚያ ወዲያ የአ​ሞ​ንን ልጆች ይረዱ ዘንድ ፈሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለአድርአዛርም የሚገብሩ ነገሥታት ሁሉ በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ ከእስራኤል ጋር ታረቁ፥ ገበሩላቸውም። ሶርያውያንም ከዚያ ወዲያ የአሞንን ልጆች ይረዱ ዘንድ ፈሩ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 10:19
12 Referencias Cruzadas  

ዳዊት በተጨማሪ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛት መልሶ ለመያዝ በሄደ ጊዜ፥ የጾባን ንጉሥ የረሖብን ልጅ ሀዳድዔዜርን ወጋው።


ከዚያም የደማስቆ ክፍል በሆነው የሶርያውያን ግዛት የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ። ሶርያውያን ተገዙለት፤ ገበሩለትም። ጌታም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።


የሶርያ ንጉሥ ቤንሀዳድ መላ ሠራዊቱን በአንድነት ሰበሰበ፤ ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ባሉአቸው ሠላሳ ሁለት ነገሥታት ተደግፎ በመዝመት የእስራኤል ዋና ከተማ የሆነችውን ሰማርያን ከቦ አደጋ ጣለባት።


የአድርአዛርም ባርያዎች በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ ከዳዊት ጋር ታረቁ፥ ገበሩለትም፤ ሶርያውያንም ከዚያ ወዲያ የአሞንን ልጆች ለመርዳት እንቢ አሉ።


አቤቱ ጌታ፥ እጅህ ከፍ ከፍ አለች አላዩም፤ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፤ እሳትም ጠላቶችህን ትበላለች።


በዚያን ጊዜም ኢያሱ ተመልሶ አሦርን ያዘ፥ ንጉሥዋንም በሰይፍ ገደለ፤ አሦርም አስቀድሞ የእነዚህ መንግሥታት ዋና ከተማ ነበረች።


ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ! ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን! ወዮልሽ! ወዮልሽ! በአንድ ሰዓት ውስጥ ፍርድሽ ይፈጸማልና፤” እያሉ ይናገራሉ።


አዶኒቤዜቅም፥ “የእጃቸውና የእግራቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር የወደቀ ፍርፋሪ ይለቃቅሙ ነበር፤ አሁን ግን እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የፈጸምሁትን አመጣብኝ” አለ፤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፤ በዚያም ሞተ።