2 ሳሙኤል 1:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ዳዊት ከጉልማሶቹ አንዱን ጠርቶ፥ “በል ቅረብና ግደለው!” አለው። እርሱም መታው፤ ገደለውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም ከጕልማሶቹ አንዱን ጠርቶ፣ “በል ቅረብና ውደቅበት” አለው። እርሱም መታው፤ ሞተም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ዳዊት ከተከታዮቹ አንዱን ጠርቶ “ግደለው!” ሲል አዘዘው፤ ሰውየውም ዐማሌቃዊውን መትቶ ገደለው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ከብላቴኖቹ አንዱን ጠርቶ፥ “ሂድና ግደለው” አለው፤ ገደለውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ከጕልማሶቹ አንዱን ጠርቶ፦ ወደ እርሱ ቅረብና ውደቅበት አለው። እርሱም መታው፥ ሞተም። |
ከዚህም በኋላ ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ሺምዒን እንዲገድል ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ ሺምዒን ገደለው፤ በዚህም ዓይነት መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ የጸና ሆነ።