2 ነገሥት 8:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ አዛሄል ተመልሶ ሲመጣ “ኤልሳዕ ምን አለህ?” ሲል ቤንሀዳድ ጠየቀው። አዛሄልም “አንተ በእርግጥ እንደምትድን ነግሮኛል” ሲል መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አዛሄል ከኤልሳዕ ዘንድ ወጥቶ ወደ ጌታው ተመለሰ፤ ቤን ሃዳድም፣ “ለመሆኑ ኤልሳዕ ምን አለህ?” ሲል ጠየቀው፤ አዛሄልም፣ “በርግጥ ከበሽታህ እንደምትድን ነግሮኛል” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ አዛሄል ተመልሶ ሲመጣ “ኤልሳዕ ምን አለህ?” ሲል ቤንሀዳድ ጠየቀው። አዛሄልም “አንተ በእርግጥ እንደምትድን ነግሮኛል” ሲል መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኤልሳዕም ወጥቶ ወደ ጌታው መጣ፤ እርሱም፥ “ኤልሳዕ ምን አለህ?” አለው፤ እርሱም አለው፥ “መዳንን ትድናለህ በለው አለኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኤልሳዕም ርቆ ወደ ጌታው መጣ፤ እርሱም “ኤልሳዕ ምን አለህ?” አለው። እርሱም “እንድትፈወስ ነገረኝ፤” አለው። |
ነገር ግን በማግስቱ አዛሄል ብርድልብስ ወስዶ ውሃ ውስጥ ነከረ፤ በዚያም ንጉሡን አፍኖ ገደለው። አዛሄልም በቤንሀዳድ እግር ተተክቶ የሶርያ ንጉሥ ሆነ።