La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከነቢያቱም አንዱ ኤልሳዕን አብሮአቸው እንዲሄድ ጠየቀው፤ ኤልሳዕም በጥያቄው ተስማማ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከመካከላቸውም አንዱ፣ “አንተስ ከአገልጋዮችህ ጋራ አትመጣምን?” አለው። ኤልሳዕም፣ “ዕሺ እመጣለሁ” አለ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከነቢያቱም አንዱ ኤልሳዕን አብሮአቸው እንዲሄድ ጠየቀው፤ ኤልሳዕም በጥያቄው ተስማማ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ፥ “አንተ ደግሞ ከእኛ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር ለመ​ሄድ ና” አለ። ኤል​ሳ​ዕም፥ “እሽ እኔም እመ​ጣ​ለሁ” አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእነርሱም አንዱ “አንተ ደግሞ ከእኛ ከባሪያዎችህ ጋር ለመሄድ ፍቀድ፤” አለ። እርሱም “እሄዳለሁ” አለ።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 6:3
8 Referencias Cruzadas  

የልጁ እናት ግን ኤልሳዕን “በምተማመንበት በሕያው እግዚአብሔር ስምና በነፍስህ እምላለሁ፤ ከቶ አንተን ትቼ አልሄድም!” አለችው፤ ስለዚህ እርሷን ተከትሎ ለመሄድ ተነሣ፤


ንዕማንም “እንግዲያውስ እባክህ ስድስት ሺህ ብር ልስጥ” ሲል መለሰለት፤ በዚህም አሳቡ በመጽናት ብሩን በሁለት ከረጢት ሞልቶ ከሁለት መለወጫ ልብሶች ጋር በሁለት አገልጋዮች አስይዞ ከግያዝ ቀድመው በፊት በፊቱ እንዲሄዱ አደረገ።


ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሄደን ዛፍ በመቁረጥ የምንኖርበት ቤት በዚያ እንድንሠራ ፍቀድልን!” አሉት። ኤልሳዕም “እሺ መልካም ነው!” አላቸው።


አብረውም ሄዱ፤ ወደ ዮርዳኖስም በደረሱ ጊዜ ዛፍ የመቁረጥ ተግባራቸውን ጀመሩ፤


አሁንም፥ እባካችሁ፥ ወደ እኔ ተመልከቱ፥ በፊታችሁም ሐሰት አልናገርም።


ሙሴም እንዲህ አለው፦ “አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህ፥ ከዚህ አታውጣን።


ስለዚህ ሁለቱ ለመብላትና ለመጠጣት አብረው ተቀመጡ። የልጂቷም አባት፥ “እባክህ ዛሬም እዚሁ አድረህ ተደሰት” አለው።


ባራቅም፥ “አብረሽኝ የምትሄጂ ከሆነ እሄዳለሁ፤ አብረሽኝ የማትሄጂ ከሆነ ግን አልሄድም” አላት።