2 ነገሥት 24:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናቡከደነፆር ኢኮንያንን አስሮ ከነእናቱ ከሚስቶቹ፥ ባለሟሎቹ ከሆኑ ባለሥልጣኖችና ከይሁዳ ታላላቅ ሰዎች ጋር በአንድነት ሰብስቦ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናቡከደነፆር ዮአኪንን ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ እንዲሁም የንጉሡን እናት፣ ሚስቶቹን፣ ሹማምቱና በአገር የታወቁትን ታላላቅ ሰዎችም ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ወሰደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡከደነፆር ኢኮንያንን አስሮ ከነእናቱ ከሚስቶቹ፥ ባለሟሎቹ ከሆኑ ባለሥልጣኖችና ከይሁዳ ታላላቅ ሰዎች ጋር በአንድነት ሰብስቦ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮአኪንንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ፤ የንጉሡንም እናት፥ የንጉሡንም ሚስቶች፥ ጃንደረቦቹንም፥ የሀገሩንም ታላላቆች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማረከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮአኪንንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ፤ የንጉሡንም እናት፥ የንጉሡንም ሚስቶች፥ ጃንደረቦቹንም፥ የአገሩንም ታላላቆች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማረከ። |
ኢኮንያን በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ስምንት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ወር ገዛ፤ እናቱም ነሑሽታ ተብላ የምትጠራ የኢየሩሳሌም ተወላጅ የሆነው የኤልናታን ልጅ ነበረች።
ዮርማሮዴቅ ኤዊልመሮዳክ በነገሠበት ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን ከእስራት በመፍታት ምሕረት አደረገለት፤ ይህም የሆነው ኢኮንያን በእስረኛነት ተማርኮ በሄደ በሠላሳ ሰባት ዓመቱ በዐሥራ ሁለተኛው ወር በሃያ ሰባተኛው ቀን ነው።
ዓመቱ ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደናፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፥ የከበረውንም የጌታን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ ወንድሙንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ።
ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያን እናቱም እቴጌይቱና ጃንደረቦቹም፥ የይሁዳና የኢየሩሳሌምም አለቆች፥ ጠራቢዎችና ብረት ሠራተኞችም ከኢየሩሳሌም ከወጡ በኋላ ነው።
ለዓመፀኛ ቤት እንዲህ በል፦ እነዚህ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ አታውቁምን? በላቸው። ንገራቸው፦ እነሆ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ንጉሥዋንና ልዑሎችዋን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ባቢሎን አመጣቸው።
እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትልቅ ክንፎች፥ ረጅም ማርገብገቢያ ያለው፥ ዝንጉርጉርና ብዙ ላባ ያለው ትልቅ ንስር ወደ ሊባኖስ መጣ፥ የዝግባንም ጫፍ ወሰደ።
በመንጠቆዎችም አድርገው በቀፎ ውስጥ አኖሩት፥ ወደ ባቢሎንም ንጉሥ አመጡት፤ ድምፁ በእስራኤል ተራሮች ላይ ዳግመኛ እንዳይሰማ ወደ እስር ቤት አመጡት።