2 ነገሥት 23:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሀያ አምስት ዓመት ነበር፤ መኖርያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ዘቢዳ ተብላ የምትጠራ የሩማ ከተማ ተወላጅ የሆነው የፐዳያ ልጅ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአቄም በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዐምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ። እናቱ ዘቢዳ ትባላለች፤ እርሷም የሩማ ተወላጅ የፈዳያ ልጅ ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ነበር፤ መኖርያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ዘቢዳ ተብላ የምትጠራ የሩማ ከተማ ተወላጅ የሆነው የፐዳያ ልጅ ነበረች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአቄምም በነገሠ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ሄልድፍ ትባል ነበር፤ እርስዋም የሩማ ሰው የፈዳያ ልጅ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ዘቢዳ ትባል ነበር፤ እርስዋም የሩማ ሰው የፈዳያ ልጅ ነበረች። |
ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ በአምላኩም በጌታ ፊት ክፉ አደረገ።
በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ ዐሥራ አንደኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ መጣ።
ስለዚህ ጌታ ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፦ “ ‘ወንድሜ ሆይ! ወዮ! እህቴ ሆይ! ወዮ!’ እያሉ አያለቅሱለትም፥ ወይም፦ ‘ጌታ ሆይ! ወዮ! ግርማዊነቱ ሆይ! ወዮ!’ እያሉ አያለቅሱለትም።