2 ነገሥት 19:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእነዚያ አገር ነዋሪዎች ኃይላቸው ተዳክሞ፥ ተስፋ በመቁረጥ እንዳያፍሩ ተደርገው በምሥራቅ ነፋስ እንደ ተመቱ፥ የመስክ አትክልቶች፥ እንደ ቀጨጩ አረንጓዴ ቡቃያዎች፥ በጣራ ላይ እንደ በቀለ ሣር ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚኖሩባቸውም ሰዎች ኀይላቸው ተሟጥጦ ዐልቋል፤ ደንግጠውም የኀፍረት ማቅ ለብሰዋል፤ ሜዳ ላይ እንደ በቀለ ተክል፣ ገና እንዳልጠነከረ የቡቃያ ሥር፣ በቤት ጣራ ላይ በቅሎ፣ ገና ሳያድግ እንደ ጠወለገ ሣርም ሆነዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነዚያ አገር ነዋሪዎች ኀይላቸው ተዳክሞ፥ ተስፋ በመቊረጥ እንዳያፍሩ ተደርገው በምሥራቅ ነፋስ እንደ ተመቱ፥ የመስክ አትክልቶች፥ እንደ ቀጨጩ አረንጓዴ ቡቃያዎች፥ በጣራ ላይ እንደ በቀለ ሣር ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም የሚኖሩባቸው ሰዎች እጆቻቸው ዝለዋል፤ ደንግጠውም አፍረዋል፤ እንደ ምድረ በዳ ሣር፥ እንደ ለምለምም ቡቃያ፥ በሰገነትም ላይ እንዳለ ሣር፥ ሳይሸት ዋግ እንደ መታውም እህል ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም የሚኖሩባቸው ሰዎች እጃቸው ዝሎአል፤ ደንግጠውም ታውከዋል፤ እንደ ምድረ በዳ ሣር፥ እንደ ለምለምም ቡቃያ፥ በሰገነትም ላይ እንዳለ ሣር፥ ሳይሸት ዋግ እንደ መታውም እህል ሆነዋል። |
ሽብር ይይዛቸዋል፤ ሥቃይና ጭንቀት ይደርስባቸዋል፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ያምጣሉ፤ እርስ በርሳቸው በድንጋጤ ይተያያሉ፤ ፊታቸውም በፍርሀት ቀይ ይሆናል።
እናንተንም የሚወጉዋችሁን የከለዳውያንን ሠራዊት ሁሉ ድል ብታደርጉ እንኳ ከእነርሱም መካከል የቆሰሉ ሰዎች ብቻ ቢቀሩ፥ እነርሱም ሁሉ ከየድንኳኖቻቸው ይነሣሉ ይህችንም ከተማ በእሳት ያቃጥላታል።’ ”
የባቢሎን ኃያላን መዋጋትን ትተዋል በምሽጎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኃይላቸውም ደክሙአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል መቀርቀሪያዎችዋም ተሰብረዋል።
ብቻ፥ በጌታ ላይ አታምፁ፤ ለእኛ እንደ እንጀራ ቁራሽ ናቸውና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ ጌታም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው።”