2 ነገሥት 16:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ኡሪያን እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ይህን የእኔን ታላቅ መሠዊያ ማለዳ ለሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት፥ በምሽት ለሚቀርበውም የእህል መባ ስለ ንጉሡና ስለ ሕዝቡ የሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል መባ የሚቀርብበትና የሕዝቡ የወይን ጠጅ መባ የሚፈስበት እንዲሆን አድርግ፤ የሚሠውትንም የእንስሶች ደም ሁሉ በእርሱ ላይ አፍስስ፤ ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ግን እኔ ራሴ የምፈልገውን ነገር የምጠይቅበት እንዲሆን አድርግ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንጉሥ አካዝ፣ ካህኑን ኦርያን እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “በዚህ በትልቁ አዲስ መሠዊያ ላይ የጧቱን የሚቃጠል መሥዋዕትና የማታውን የእህል ቍርባን፣ የንጉሡን የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን እንዲሁም የመላውን የአገሪቱን ሕዝብ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የእህልና የመጠጥ ቍርባናቸውን አቅርብ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ደምና የሌላውን መሥዋዕት ደም ሁሉ በመሠዊያው ላይ ርጨው፤ የናሱ መሠዊያ ግን እኔ መመሪያ ለመጠየቅ የምጠቀምበት ይሆናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኡሪያን እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ይህን የእኔን ታላቅ መሠዊያ ማለዳ ለሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት፥ በምሽት ለሚቀርበውም የእህል መባ ስለ ንጉሡና ስለ ሕዝቡ የሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል መባ የሚቀርብበትና የሕዝቡ የወይን ጠጅ መባ የሚፈስበት እንዲሆን አድርግ፤ የሚሠዉትንም የእንስሶች ደም ሁሉ በእርሱ ላይ አፍስስ፤ ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ግን እኔ ራሴ የምፈልገውን ነገር የምጠይቅበት እንዲሆን አድርግ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም አካዝ፥ “የሚቃጠለውን የጥዋት መሥዋዕት፥ የማታውንም የእህሉን ቍርባን፥ የንጉሡንም መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ የሕዝቡንም ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን፥ የመጠጡንም ቍርባን በታላቁ መሠዊያ ላይ አቅርብ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ደም ሁሉ፥ የሌላውንም መሥዋዕታቸውን ደም ሁሉ በእርሱ ላይ ርጭበት፤ የናሱ መሠዊያ ግን በየጥዋቱ ለእኔ ይሁን” ብሎ ካህኑን ኦርያን አዘዘው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡ አካዝም “የሚቃጠለውን የጠዋት መሥዋዕት፥ የማታውንም የእህሉን ቍርባን፥ የንጉሡንም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ ለአገሩም ሕዝብ የሚሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን የመጠጡንም ቍርባን በታላቁ መሠዊያ ላይ አቅርብ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ደም ሁሉ የሌላ መሥዋዕቱንም ደም ሁሉ ርጭበት፤ የናሱ መሠዊያ ግን እኔ እጠይቅበት ዘንድ ይሁን፤” ብሎ ካህኑን ኦርያን አዘዘው። |
ታላቁ መሠዊያ የሚገኘው በገባዖን ስለ ነበር አንድ ቀን ሰሎሞን መሥዋዕትን ለማቅረብ ወደዚያ ሄደ፤ ከዚህም በፊት በዚያ መሠዊያ ላይ አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቅርቧል።
ሑራም ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ጥልቀት፥ አራት ሜትር ከአርባ ሳንቲ ሜትር የክብ ማእከል ርዝመት፤ ዐሥራ ሦስት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ዙሪያ ያለው አንድ ክብ ገንዳ ከነሐስ ሠራ።
እንዲሁም በዚያኑ ቀን ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን አደባባይ መካከለኛ ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረገ፤ ቀጥሎም በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህል ቁርባንና የኅብረት መሥዋዕት፥ የእንስሶች ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ይህን ሁሉ መሥዋዕት መያዝ ስለማይችል ነው።
ከነሐስ ተሠርቶ ለእግዚአብሔር የተለየውም መሠዊያ በዚያ አዲስ መሠዊያና በቤተ መቅደሱ መካከል ነበር፤ አካዝም ያንን መሠዊያ አስነሥቶ እርሱ ባሠራው በአዲሱ መሠዊያ በስተ ሰሜን በኩል አኖረው፤
የአሕዛብን የማምለኪያ ስፍራዎችን ደመሰሰ፤ የድንጋይ ዐምዶችን ሰባበረ፤ አሼራ ተብላ በምትጠራው ሴት አምላክ ስም የተቀረጹትን ምስሎች ሁሉ አንኮታክቶ ጣለ፤ ሙሴ ከነሐስ ሠርቶት የነበረውን ኔሑሽታን ተብሎ የሚጠራውን የእባብ ምስል ሰባብሮ አደቀቀ፤ እስከዚያን ጊዜ ድረስ ግን እስራኤላውያን ለእርሱ ዕጣን ያጥኑለት ነበር።
ጉባኤውም ያመጡት የሚቃጠል መሥዋዕት ቍጥር ሰባ በሬዎች፥ መቶም አውራ በጎች፥ ሁለት መቶም የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ ይህ ሁሉ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ።
እጅግ ብዙ ከነበረው የሚቃጠል መሥዋዕት ጋር የአንድነቱ መሥዋዕት ስብ ነበረ፤ ለሚቃጠለውም መሥዋዕት የሚቀርበው የመጠጥ ቁርባን በዚያ ነበረ። እንዲህ ባለ መንገድ የጌታ ቤት አገልግሎት ተዘጋጀ።
በሄኖምም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆቹን በእሳት በማቃጠል እንደ መሥዋዕት አቀረበ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፥ አስማትም አደረገ፥ መተተኛም ነበረ፥ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ጌታንም ለማስቈጣት በጌታ ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ።
የያዕቆብ ቤት የሆነውን፤ ሕዝብህን ትተሃል፤ እነርሱ በምሥራቅ ሰዎች ከንቱ አምልኮ ተሞልተዋልና፤ እንደ ፍልስጥኤማውያን ያሟርታሉ፤ ከባዕዳን ጋር ተባብረዋል።