2 ነገሥት 14:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዖዝያም ቀድሞ ተይዛ የነበረችውን ኤላትን ከአባቱ ሞት በኋላ በጦር ኃይል ድል ነሥቶ በማስመለስ እንደገና ሠራት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ አሜስያስ ከአባቶቹ ጋራ ካንቀላፋ በኋላ ኤላትን እንደ ገና ሠርቶ ወደ ይሁዳ የመለሳት ይኸው ዓዛርያስ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዖዝያም ቀድሞ ተይዛ የነበረችውን ኤላትን ከአባቱ ሞት በኋላ በጦር ኀይል ድል ነሥቶ በማስመለስ እንደገና ሠራት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ከአባቶቹ ጋር ከአንቀላፋ በኋላ፥ ኤላትን ሠርቶ ወደ ይሁዳ መለሳት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ከአባቶቹ ጋር ካንቀላፋ በኋላ፥ ኤላትን ሠርቶ ወደ ይሁዳ መለሳት። |
የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ እርሱም መኖሪያውን በሰማርያ አድርጎ አርባ አንድ ዓመት ገዛ።
በዚያኑ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ ረጺን የኤላትን ከተማ አስመልሶ በቁጥጥሩ ሥር በማድረግ በዚያ የነበሩትን አይሁድ አስወጣ፤ ያንጊዜ በኤላት የሰፈሩት ኤዶማውያን እስከ አሁን በዚያ ይገኛሉ።
“እኛም ወንድሞቻችን የዔሳው ልጆች ከተቀመጡት ሴይር አልፈን፥ በዓረባ መንገድ ከኤላትና ከዔጽዮንጋብር አለፍን። ተመልሰንም በሞዓብ ምድረ በዳ መንገድ አለፍን።