ኢዩም በእስራኤል ምድር ሁሉ መልእክት አስተላለፈ፤ በዓልን የሚያመልኩ ሁሉ ተሰበሰቡ፤ አንድም እንኳ የቀረ ሰው አልነበረም፤ ሁሉም ወደ በዓል ቤተ መቅደስ ገብተው ዳር እስከ ዳር ሞሉት፤
2 ነገሥት 10:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ኢዩ የተቀደሱ አባላት ኃላፊ የሆነውን ካህን አልባሳቱን ሁሉ አውጥቶ ለበዓል አምላኪዎች ያጐናጽፋቸው ዘንድ አዘዘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዩም የልብስ ቤቱን ኀላፊ፣ “ለበኣል አገልጋዮች ሁሉ አልባሳት አውጣ” አለው፤ እርሱም አልባሳቱን አወጣላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢዩ የተቀደሱ አባላት ኀላፊ የሆነውን ካህን አልባሳቱን ሁሉ አውጥቶ ለባዓል አምላኪዎች ያጐናጽፋቸው ዘንድ አዘዘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዕቃ ቤቱንም ሹም፥ “ለበዓል አገልጋዮች ሁሉ ልብስን አውጣ” አለው። የሚያለብሳቸውንም ልብሱን አወጣላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዕቃ ቤቱንም “ለበኣል አገልጋዮች ሁሉ ልብስ አውጣ፤” አለው። ልብሱንም አወጣላቸው። |
ኢዩም በእስራኤል ምድር ሁሉ መልእክት አስተላለፈ፤ በዓልን የሚያመልኩ ሁሉ ተሰበሰቡ፤ አንድም እንኳ የቀረ ሰው አልነበረም፤ ሁሉም ወደ በዓል ቤተ መቅደስ ገብተው ዳር እስከ ዳር ሞሉት፤
ከዚህም በኋላ ኢዩ ራሱ የሬካብ ልጅ ከሆነው ከኢዮናዳብ ጋር አብሮ ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ፤ በዚያም ለሕዝቡ “እንግዲህ በዚህ የሚገኙት የበዓል አምላኪዎች ብቻ መሆናቸውንና እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንድም አለመኖሩን በሚገባ አረጋግጡ” ሲል ተናገረ፤