2 ነገሥት 10:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ሁሉ እግዚአብሔር ስለ አክዓብ ትውልድ የተናገረው ቃል እውነት መሆኑን ያስረዳል፤ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በነቢዩ ኤልያስ አማካይነት የተናገረውን ቃል ፈጽሞታል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ እግዚአብሔር በአክዓብ ቤት ላይ ከተናገረው ቃል አንዲቱ እንኳ በምድር ላይ ወድቃ እንደማትቀር ዕወቁ። እግዚአብሔር በባሪያው በኤልያስ የተናገረውን ፈጽሟል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሁሉ እግዚአብሔር ስለ አክዓብ ትውልድ የተናገረው ቃል እውነት መሆኑን ያስረዳል፤ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በነቢዩ ኤልያስ አማካይነት የተናገረውን ቃል ፈጽሞታል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ እግዚአብሔር በአክአብ ቤት ላይ ከተናገረው ከእግዚአብሔር ቃል በምድር ላይ አንዳች እንዳይወድቅ አሁን ዕወቁ፤ እግዚአብሔር በባሪያው በኤልያስ ቃል የተናገረውን አድርጎአል” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በአክዓብ ቤት ላይ ከተናገረው ከእግዚአብሔር ቃል በምድር ላይ አንዳች እንዳይወድቅ አሁን እወቁ፤ እግዚአብሔር በባሪያው በኤልያስ የተናገረውን አድርጎአል፤” አላቸው። |
እነዚህም በእነዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰባተኛውም ቀን ተጋጠሙ፤ የእስራኤልም ልጆች ከሶርያውያን በአንድ ቀን መቶ ሺህ እግረኛ ገደሉ።
እዚያም በደረሱ ጊዜ ኢዩ አንድም ሳያስቀር የአክዓብን ዘመዶች በሙሉ ፈጀ፤ ይህም ሁሉ የሆነው እግዚአብሔር በነቢዩ ኤልያስ አማካይነት በተናገረው ቃል መሠረት ነበር።
ይህንንም ሁሉ ለኢዩ በነገሩት ጊዜ ኢዩ እንዲህ አለ፤ “ይህ ሁሉ የተፈጸመው እግዚአብሔር በአገልጋዩ ቴስቢያዊው በኤልያስ አማካይነት አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ነው፤ ይኸውም ‘የኤልዛቤልም ሬሳ በኢይዝራኤል ግዛት ውሾች ይበሉታል፤
ነገር ግን ለአገልጋዮቼ ለነቢያት ያዘዝኳቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? ከዚያ እነርሱም ተጸጽተው፦ “የሠራዊት ጌታ በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ሊያደርግብን ያሰበውን እንዲሁ አድርጎብናል” በማለት ተቀበሉ።