Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 21:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እነዚህም የአውራጆች አለቆች ጉልማሶች ከከተማይቱ ወጡ፤ ሠራዊትም ተከተላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እንዲህም በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሰውየውን ገደልኸው፤ ደግሞ ርስቱን ልትወስድ?’ ከዚያም እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ቦታ የአንተንም ደም ውሾች እንዲሁ ይልሱታል!’ ”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እኔ እግዚአብሔር ስለ እርሱ የምለው ይህ ነው ‘ናቡቴን መግደልህ አንሶህ ሀብቱንም ልትወርስበት ነውን?’ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ስፍራ እንዲሁም የአንተን ደም ይልሱታል!’ ”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እነ​ዚ​ህም የአ​ው​ራ​ጃ​ዎች አለ​ቆች ጐል​ማ​ሶች ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጡ፤ ሠራ​ዊ​ትም ተከ​ተ​ላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እነዚህም የአውራጆች አለቆች ጕልማሶች ከከተማይቱ ወጡ፥ ሠራዊትም ተከተላቸው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 21:19
23 Referencias Cruzadas  

እግዚእብሔርም፦ “ዕራቁትህን እንደሆንህ ማን ነገረህ? እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ ከእርሱ በላህን?” አለው።


ጌታ እንዲህ ይላል፤ “እነሆ ከራስህ ቤት ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ ዐይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለአንተ ቅርብ ለሆነ ሰው ለአንዱ እሰጣለሁ፤ እርሱም በቀን ብርሃን ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል።


ታዲያ በፊቱ ክፉ ነገር በማድረግ፥ የጌታን ቃል ያቃለልኸው ስለምንድን ነው? ሒታዊውን ኦርዮን በሰይፍ መታህ፤ ሚስት እንድትሆንህም ሚስቱን ወሰድሃት፤ እርሱንም በአሞናውያን ሰይፍ ገደልኸው።


ሠረገላውም በሰማርያ ኲሬ ታጠበ፤ ጌታም አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ደሙን ውሾች ላሱት፤ በዚያም ኲሬ ጋለሞታዎች ታጠቡበት።


ይህም ሁሉ እግዚአብሔር ስለ አክዓብ ትውልድ የተናገረው ቃል እውነት መሆኑን ያስረዳል፤ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በነቢዩ ኤልያስ አማካይነት የተናገረውን ቃል ፈጽሞታል።”


የኢዩ ደብዳቤ እንደ ደረሳቸው የሰማርያ መሪዎች ሰባውንም የአክዓብ ተወላጆች በሙሉ ገደሉ፤ ራሶቻቸውንም በመቁረጥ በቅርጫት ሞልተው በኢይዝራኤል ወደነበረው ወደ ኢዩ ላኩለት።


ወዲያውኑም ኤልሳዕን ይዞ የሚመጣ መልእክተኛ ላከ። በዚህም ጊዜ ኤልሳዕ ሊጐበኙት ከመጡ ጥቂት ሽማግሌዎች ጋር በቤት ውስጥ ነበር፤ የንጉሡ መልእክተኛ ከመድረሱም በፊት ኤልሳዕ ሽማግሌዎቹን “ያ ነፍሰ ገዳይ እኔን ለማስገደል አንድ ሰው ልኮአል! እነሆ፥ እርሱ እዚህ በሚደርስበት ጊዜ በሩን ዝጉ፤ ወደ ውስጥም እንዲገባ አትፍቀዱለት፤ ንጉሡም እርሱን ተከትሎ መጥቶ በኋላው ይገኛል” አላቸው።


ፍሬዋን ያለ ዋጋ በልቼ፥ የባለቤቶችንም ነፍስ አሳዝኜ እንደሆነ፥


ጌታ እንዲህ አለ፦ ከባሳን አመጣቸዋለሁ፥ ከባሕርም ጥልቅ እመልሳቸዋለሁ፥


ደምን የሚበቀል እርሱ አስቦአልና፥ የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና።


አሕዛብ በሠሩት ጉድጓድ ወደቁ፥ በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደች።


ነቢዩ ኤርምያስ እነዚህን ቃላት ሁሉ ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ነገረው፤


መስፍኑ ሕዝቡን ከይዞታቸው ሊጨቁናቸው ርስታቸውን አይውሰድባቸው፤ ሕዝቤ ሁሉ ከይዞታቸው እንዳይነቀሉ ከገዛ ይዞታው ለልጆቹ ርስትን ይስጥ።


ከተማን በደም ለሚሠራ፥ ከተማንም በበደል ለሚመሠርት ወዮለት!


ከክፉ ለመታደግ ጐጆውን በከፍታ ላይ በማድረግ፥ ለቤቱ ክፉ ትርፍን የሚሰበስብ ወዮለት!


በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋል፤ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።


አዶኒቤዜቅም፥ “የእጃቸውና የእግራቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር የወደቀ ፍርፋሪ ይለቃቅሙ ነበር፤ አሁን ግን እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የፈጸምሁትን አመጣብኝ” አለ፤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፤ በዚያም ሞተ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos