La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዮሐንስ 1:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሁንም እመቤት ሆይ! አዲስን ትእዛዝ አልጽፍልሽም ነገር ግን ከመጀመሪያ ጀምሮ የነበረውን ነው፥ ይህም እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁንም እመቤት ሆይ፤ እለምንሻለሁ፤ ከመጀመሪያ የነበረችውን እንጂ አዲስ ትእዛዝ አልጽፍልሽም፤ ይኸውም እርስ በርሳችን እንዋደድ ዘንድ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እመቤት ሆይ፥ አሁንም ዐደራሽን፥ ይህ የምጽፍልሽ አዲስ ትእዛዝ አይምሰልሽ፤ አሁን የምጽፍልሽ “እርስ በርሳችን እንዋደድ” የሚለውን ከመጀመሪያ አንሥቶ በእኛ ዘንድ የነበረውን ትእዛዝ ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሁንም እመቤት ሆይ! እርስ በርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ፤ ይህች ከመጀመሪያ በእኛ ዘንድ የነበረች ትእዛዝ ናት እንጂ አዲስ ትእዛዝን እንደምጽፍልሽ አይደለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሁንም፥ እመቤት ሆይ፥ እርስ በርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ፤ ይህች ከመጀመሪያ በእኛ ዘንድ የነበረች ትእዛዝ ናት እንጂ አዲስ ትእዛዝን እንደምጽፍልሽ አይደለም።

Ver Capítulo



2 ዮሐንስ 1:5
17 Referencias Cruzadas  

“ትእዛዜ ይህች ናት፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ።


እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ አዛችኋለሁ።


የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥


ክርስቶስም እንዳፈቀራችሁ፥ ስለ እናንተም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ ያለው መባንና መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ፥ በፍቅር ተመላለሱ።


እናንተ ራሳችሁ የእርስ በእርስ መዋደድን በእግዚአብሔር ተምራችኋልና፥ ስለ ወንድማማች መዋደድ ማንም ሊጽፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፤


እርስ በርሳችሁ መዋደዳችሁን ቀጥሉ።


ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።


እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችነት መዋደድ፥ በወንድማማችነትም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።


ከመጀመሪያ የሰማችሁት መልእክት ይህ ነውና፥ እርሱም፦ እርስ በርሳችን እንዋደድ፥


ትእዛዚቱም ይህች ናት፥ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥም እንድናምንና፥ እርሱም እንዳዘዘን እርስ በርሳችን እንድንዋደድ ነው።


ማንም፦ “እግዚአብሔርን እወደዋለሁ” ቢል ወንድሙን ግን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወድ አይችልምና።


ሽማግሌው፥ ለተመረጠችው እመቤትና ለልጆችዋ፥ በእውነት ለምወዳቸው፥ እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ለሚወዱአቸው፥