Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዮሐንስ 4:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ማንም፦ “እግዚአብሔርን እወደዋለሁ” ቢል ወንድሙን ግን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወድ አይችልምና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ማንም፣ “እግዚአብሔርን እወድደዋለሁ” እያለ ወንድሙን ቢጠላ፣ እርሱ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድድ ያላየውን እግዚአብሔርን መውደድ አይችልምና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን የሚጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ከሆነ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወድ አይችልም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?

Ver Capítulo Copiar




1 ዮሐንስ 4:20
9 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ማንም የዚህ ዓለም ሀብት ቢኖረው፥ ወንድሙም ተቸግሮ አይቶ ባይራራለት፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?


በብርሃን አለሁ እያለ ወንድሙን ግን የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ ውስጥ ነው።


እግዚአብሔርን ያየው ማንም የለም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል፥ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል።


“አውቀዋለሁ” የሚል፥ ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ እርሱ ሐሰተኛ ነው፥ እውነትም በእርሱ ዘንድ የለም።


ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ ይኖራል፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ ጨለማው ዐይኖቹን ስላሳወረው ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።


እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩትም በእርሱ በማመናችሁ መግለጽ በማይቻልና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ብሎአችኋል።


ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን እያልን በጨለማ ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤


እርስ በርሳችሁ ብትዋድዱ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።”


ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ዘንድ የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios