2 ቆሮንቶስ 8:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛም ስለምናገለግለው ስለዚህ የቸርነት ስጦታ ማንም እንዳይነቅፈን እንጠነቀቃለን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ በምናከናውነው የቸርነት ሥራ አንዳች ነቀፋ እንዳይገኝብን እንጠነቀቃለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን በልግሥና የተሰጠውን ገንዘብ ስናስተዳድር ምንም ዐይነት ነቀፌታ እንዳይደርስብን እንጠነቀቃለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለምናገለግለው ስለዚህ ለጋስ ስጦታ ማንም እንዳይነቅፈን እንጠነቀቃለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለምናገለግለው ስለዚህ ለጋስ ስጦታ ማንም እንዳይነቅፈን እንጠነቀቃለን፤ |
ነገር ግን በሚመኩበት ሥራ ከእኛ እኩል በአቻነት ለመቆጠር የሚፈልጉ ሰዎችን ምክንያት ለማሳጣት፥ አሁን የማደርገውን ወደፊትም እገፋበታለሁ።
ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የጌታን የራሱን ክብርና የእኛን በጎ ፈቃድ ለማሳየት በምናገለግለው በዚህ የቸርነት ሥራ ከእኛ ጋር አብሮን እንዲሄድ በአብያተ ክርስቲያናት ተመርጧል።