2 ቆሮንቶስ 8:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ ባለው ባለው መጠን ተቀባይነት ይኖረዋል እንጂ የሌላውን አይጠበቅበትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመስጠት በጎ ፈቃድ ካለን ስጦታው ተቀባይነት የሚያገኘው ባለን መጠን ስንሰጥ እንጂ፣ በሌለን መጠን ለመስጠት ስንሞክር አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመስጠት መልካም ፈቃድ ካለ የሰው ልግሥና ተቀባይነት የሚያገኘው ባለው መጠን ሲሰጥ እንጂ በሌለው መጠን ሲሰጥ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚቻለው መጠን ቢሰጥ ይመሰገናል፤ በማይቻለውም መጠን አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ እንዳለው መጠን የተወደደ ይሆናል እንጂ እንደሌለው መጠን አይደለም። |
ከእስራኤል ልጆች ልባቸው ያነሣሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ጌታ በሙሴ እጅ እንዲሠራ ላዘዘው ሥራ ሁሉ የሚሆን ስጦታ በፈቃዳቸው ለጌታ አመጡ።
ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የጌታን የራሱን ክብርና የእኛን በጎ ፈቃድ ለማሳየት በምናገለግለው በዚህ የቸርነት ሥራ ከእኛ ጋር አብሮን እንዲሄድ በአብያተ ክርስቲያናት ተመርጧል።