2 ቆሮንቶስ 6:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለእናንተም አባት እሆናለሁ፤ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ፤” ይላል ሁሉንም የሚገዛ ጌታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔ አባት እሆናችኋለሁ፤ እናንተም፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ትሆናላችሁ፤ ይላል ሁሉን የሚችል ጌታ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ አባታችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ትሆናላችሁ፥ ይላል ሁሉን ቻይ አምላክ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባት እሆናችኋለሁ፤ እናንተም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ትሆኑኛላችሁ አለ ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር።” |
አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል። በደል በሚፈጽምበትም ጊዜ ሰዎች በሚቀጡበት በትር እቀጣዋለሁ፤ የሰው ልጆችም በዐለንጋ እንደሚገረፉ እገርፈዋለሁ።
እኔ ግን፦ “‘ከወንዶች ልጆች ጋር እንዴት አስቀምጥሻለሁ? ያማረችውንስ ምድር እጅግ የከበረችውን የአሕዛብን ርስት እንዴት እሰጥሻለሁ? ብዬ ነበር። ደግሞ፦ አባቴ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ እኔንም ከመከተል አትመለሽም ብዬ ነበር።
በልቅሶ ይወጣሉ፤ እኔንም በመማፀናቸው እየመራሁ እመልሳቸዋለሁ፤ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስኬዳቸዋለሁ፤ በእርሱም አይሰናከሉም፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ ኤፍሬምም በኩሬ ነውና።