2 ቆሮንቶስ 5:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዎ፥ ታምነናል፤ ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በጌታ ዘንድ መኖር እንመርጣለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሥጋ ተለይተን ከጌታ ጋራ መኖርን እንደምንመርጥ ርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ እንደ መኖሪያችን ከሆነው ሥጋችን ተለይተን ከጌታ ጋር ለመሆን እንመኛለን፤ ስለዚህ በመተማመን እንኖራለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታምነናል፤ ይልቁንም ከሥጋችን ተለይተን ወደ ጌታችን እንሄዳለንና ደስ ይለናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታምነናል ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በስደት መኖር በጌታም ዘንድ ማደር ደስ ይለናል። |
አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር በፊት ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ፥ የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ።
ጳውሎስ ግን መልሶ “እያለቀሳችሁ ልቤንም እየሰበራችሁ ምን ማድረጋችሁ ነው? እኔ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞት እንኳ ተሰናድቼአለሁ እንጂ ለእስራት ብቻ አይደለም፤” አለ።
ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ቢገለጥ ግን እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና።