‘በጌታ ቤት አለቃ ሆነህ እያበደ ትንቢት የሚናገርን ሰው ሁሉ በመንቈርና በዛንጅር አስረህ እንድታኖረው ጌታ በካህኑ በዮዳሄ ፋንታ ካህን አድርጎሃል።
2 ቆሮንቶስ 5:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አእምሮችንን የሳትን ብንሆን፥ የሳትነው ለእግዚአብሔር ነው፤ ጤነኞችም ብንሆን ለእናንተ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአእምሮ ውጭ ብንሆን ለእግዚአብሔር ብለን ነው፤ ባለአእምሮም ብንሆን ለእናንተ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እብዶች ብንሆን ለእግዚአብሔር ስንል ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆንም ለእናንተ ስንል ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ ሰነፎች ብንሆንም፥ ስንፍናችን ለእግዚአብሔር ነው፤ ዐዋቂዎች ብንሆንም ዐዋቂነታችን ለእናንተ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እብዶች ብንሆን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆን፥ ለእናንተ ነው። |
‘በጌታ ቤት አለቃ ሆነህ እያበደ ትንቢት የሚናገርን ሰው ሁሉ በመንቈርና በዛንጅር አስረህ እንድታኖረው ጌታ በካህኑ በዮዳሄ ፋንታ ካህን አድርጎሃል።
እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ እንደሰጣችሁ እምነት መጠን፥ በረጋ አእምሮ አስቡ እንጂ ማሰብ ከሚገባችሁ በላይ ራሳችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንዳታስቡ በተሰጠኝ ጸጋ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ እናገራለሁና።
በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ! ይህ እናንተ ግድ ስላላችሁኝ የሆነ ነው። እኔ ከምንም የማልቆጠር ብሆን እንኳን፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አላንስምና፥ በእርግጥም እናንተ ስለ እኔ መናገር ይገባችሁ ነበር።
ልመካ ብፈልግ አልሞኝም፤ ምክንያቱም የምናገረው እውነት ነው፤ ነገር ግን ማንም ስለ እኔ ከሚያየውና ከሚሰማው ባለፈ የበለጥኩ አድርጎ እንዳያስበኝ ይህን ከመናገር እቆጠባለሁ።
እንግዲያስ ጽፌው እንኳን ቢሆን ኖሮ፥ ስለ እኛ ያላችሁ ትጋት በእናንተ በኩል በእግዚአብሔር ፊት እንዲገለጥ እንጂ፥ ስለ በደለኛ ወይም ስለ ተበዳይ አይደለም የጻፍኩት።
አሁን በመከራዬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ አካሉም ስለ ሆነችው ስለ ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ ካለፈባቸው መከራዎች መካከል የጐደሉትን በሥጋዬ እፈጽማለሁ።
ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ፥ በብዙም መረዳት እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ ስለ እናንተ ስንል በእናንተ መካከል ምን ዓይነት ሰዎች እንደ ነበርን እናንተው ታውቃላችሁ።