ሙሴ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ወደ ጌታ በገባ ጊዜ፥ እስኪ ወጣ ድረስ መሸፈኛውን አነሣ፤ በወጣም ጊዜ ለእስራኤል ልጆች የታዘዘውን ነገር ነገራቸው።
2 ቆሮንቶስ 3:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሰው ወደ ጌታ ፊቱን ሲያዞር መጋረጃው ይወገዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን አንድ ሰው ወደ ጌታ ዘወር ሲል መሸፈኛው ይወገዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሰው ወደ ጌታ ሲመለስ “መሸፈኛው ይወገዳል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እግዚአብሔር በተመለሱ ጊዜ ግን ያ መጋረጃ ከእነርሱ ይርቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ጌታ ግን ዘወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል። |
ሙሴ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ወደ ጌታ በገባ ጊዜ፥ እስኪ ወጣ ድረስ መሸፈኛውን አነሣ፤ በወጣም ጊዜ ለእስራኤል ልጆች የታዘዘውን ነገር ነገራቸው።
እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ ‘ጌታን እወቅ’ ብሎ ከእንግዲህ ወዲህ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል ጌታ። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስምና።”
የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ከሰማህ፥ በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ለመጠበቅ፥ በፍጹምም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ወደ ጌታ ወደ አምላክህ ተመለስ።