2 ቆሮንቶስ 1:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ እንዲህ ካለው የሞት አደጋ አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ወደፊትም ደግሞ እንደሚያድነን ተስፋችንን በእርሱ ላይ ጥለናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ እንዲህ ካለው የሞት አደጋ አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ወደ ፊትም ደግሞ እንደሚያድነን ተስፋችንን በርሱ ላይ ጥለናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እርሱ ለሞት ከሚያደርስ አደጋ አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ደግሞም እንደሚያድነን ተስፋችን በእርሱ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም እንዲህ ካለ ሞት አዳነን፤ ያድነንማል፤ አሁንም እንደሚያድነን እርሱን እንታመናለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ይህን ከሚያህል ሞት አዳነን፥ ያድነንማል፤ እናንተም ደግሞ ስለ እኛ እየጸለያችሁ አብራችሁ ስትረዱን፥ በብዙ ሰዎች በኩል ስለ ተሰጠን ስለ ጸጋ ስጦታ ብዙዎች ስለ እኛ ያመሰግኑ ዘንድ፥ ወደ ፊት ደግሞ እንዲያድን በእርሱ ተስፋ አድርገናል። |
እንግዲህ እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸው፥ እንዲሁም በደለኞችን እንዴት በቅጣት ስር ለፍርድ ቀንም ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።
ከአንበሳ መዳፍና ከድብ መንጋጋ ያዳነኝ ጌታ አሁንም ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሲል ዳዊት ተናገረ። ሳኦልም ዳዊትን፥ “ሂድ፤ ጌታ ካንተ ጋር ይሁን!” አለው።
ከዚህ በኋላ ሳሙኤል አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አቆመው፤ “ጌታ እስከ አሁን ድረስ ረድቶናል” ሲል ስሙን “አቤንኤዘር” ብሎ ጠራው።