2 ዜና መዋዕል 9:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኦፊርም ወርቅ ያመጡ የኪራም ባርያዎችና የሰሎሞን ባርያዎች የሰንደል እንጨትና የከበረ ዕንቁ ደግሞ አመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኪራም ሰዎችና የሰሎሞን ሰዎች ከኦፊር ወርቅ እንደዚሁም ሰንደልና የከበሩ ድንጋዮች አመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኦፊር ወርቅ ያመጡ የንጉሥ ኪራምና የንጉሥ ሰሎሞን ሰዎች ከዚያው ከኦፊር የሰንደል እንጨትና ዕንቊ ለሰሎሞን አምጥተውለት ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኪራም አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮችም ከሴፌር ለሰሎሞን ወርቅ አመጡ፤ የሰንደል እንጨትና የከበረ ዕንቍም ደግሞ አመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኦፊርም ወርቅ ያመጡ የኪራም ባሪያዎችና የሰሎሞን ባሪያዎች የሰንደል እንጨትና የከበረ ዕንቍ ደግሞ አመጡ። |
ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመት ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር።
ደግሞም ባርያዎችህ ከሊባኖስ እንጨት መቁረጥ እንደሚያውቁ እኔ አውቃለሁና ከሊባኖስ የዝግባና የጥድ የሰንደልም እንጨት ላክልኝ፤ እነሆ፥ ባርያዎቼ ከባርያዎችህ ጋር በመሆን
ኪራምም መርከቦችንና የባሕርን ነገር የሚያውቁትን መርከበኞች በባርያዎቹ እጅ ላከለት፤ እነርሱም ከሰሎሞን ባርያዎች ጋር ወደ ኦፊር መጡ፥ ከዚያም አራት መቶ ኀምሳ መክሊት ወርቅ ወስደው ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን አመጡ።
ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለጌታ ቤትና ለንጉሡ ቤት እርከኖችን፥ ለመዘምራኑም መሰንቆና በገና ሠራ፤ እንደዚህም ያለ በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም ነበር።
ለንጉሡም መቶ ሀያ መክሊት ወርቅ፥ እጅግም ብዙ ሽቶ የከበረም ዕንቁ ሰጠችው፤ የሳባም ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ ሽቶ ከቶ አልነበረም።