2 ዜና መዋዕል 7:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዝናብ እንዳይወርድ ሰማያቱን ብዘጋ፥ ወይም ምድሪቱን እንዲበላ አንበጣን ባዝዘው፥ ወይም በሕዝቤ ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማያትን በምዘጋበት ጊዜ ወይም ምድሪቱን እንዲበላ አንበጣ በማዝዝበት ጊዜ፣ ወይም በሕዝቤ ላይ ቸነፈር በምሰድድበት ጊዜ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማያትን በምዘጋበት ጊዜ፥ ወይም ሰብሉን እንዲበላ አንበጣ በምልክበት ጊዜ፥ ወይም ቸነፈር በሕዝቤ ላይ በማወርድበት ጊዜ ሁሉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዝናብ እንዳይወርድ ሰማያቱን ብዘጋ፥ ወይም የሚያፈራውን እንጨት ሁሉ ይበላ ዘንድ አንበጣን ባዝዘው፥ ወይም በሕዝቤ ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዝናብ እንዳይወርድ ሰማያቱን ብዘጋ፥ ወይም ምድሪቱን ይበላ ዘንድ አንበጣን ባዝዘው፥ ወይም በሕዝብ ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥ |
“እኔ ደግሞ መከር ሳይደርስ ገና ከሦስት ወር በፊት ዝናብ ከለከልኋችሁ፤ በአንድም ከተማ ላይ አዘነብሁ፥ በሌላውም ከተማ ላይ እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ በአንድ ወገን ባለው መሬት ዘነበ፥ ባልዘነበበትም ወገን ያለው መሬት ደረቀ።
ነገር ግን በእውነት እላችኋለሁ፤ በኤልያስ ዘመን ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ሰማይ ተዘግቶ ሳለ፥ በምድር ሁሉ ላይ ብርቱ ራብ በነበረ ጊዜ፥ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ፤
የጌታም ቁጣ በላያችሁ እንዳይነድ፤ እርሱም ዝናብ እንዳይከለክላችሁ፤ ምድሪቱም ፍሬ እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤ እናንተም ጌታ ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ወዲያውኑ ትጠፋላችሁ።”
እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን የመዝጋት ሥልጣን አላቸው፤ ውሃዎችንም ወደ ደም ለመለወጥ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ምድርን የመምታት ሥልጣን አላቸው።
“በፊላደልፊያም ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ ‘ቅዱስና እውነተኛ የሆነው፥ የዳዊትም መክፈቻ ያለው፥ ሲከፍትም፥ ማንም የማይዘጋው፤ ሲዘጋም ማንም የማይከፍተው፤ እርሱ እንዲህ ይላል’፦