2 ዜና መዋዕል 6:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን፥ አቤቱ አምላኬ ሆይ! ወደ ባርያህ ጸሎትና ልመና ተመልከት፥ ባርያህም በፊትህ የሚጸልየውን ጸሎትና ጥሪውን ስማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ የባሪያህን ጸሎትና ስለ ምሕረት ያቀረበውን ልመና አድምጥ፤ ባሪያህ በፊትህ የሚያቀርበውን ጩኸትና ጸሎት ስማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፥ ወደ እኔ ወደ አገልጋይህ ጸሎትና ልመና ተመልከት፤ በፊትህም የምጸልየውን ጸሎትና ጥሪ አዳምጥ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ ወደ ባሪያህ ጸሎትና ልመና ተመልከት፤ ባሪያህ በዚች ዕለት በፊትህ የሚጸልየውን ጸሎትና ልመናውን ስማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን፥ አቤቱ አምላኬ ሆይ! ወደ ባሪያህ ጸሎትና ልመና ተመልከት፤ ባሪያህም በፊትህ የሚጸልየውን ጸሎትና ጥሪውን ስማ። |
“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለ ሰማይ አንተን መያዝ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ ይሆን?
ባርያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውን ጸሎት እንድትሰማ በዚያ ስሜ ይሆናል ወዳልኸው ስፍራ፥ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ቀንና ሌሊት የተገለጡ ይሁኑ።