Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 6:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ባርያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውን ጸሎት እንድትሰማ በዚያ ስሜ ይሆናል ወዳልኸው ስፍራ፥ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ቀንና ሌሊት የተገለጡ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስምህ እንደሚጠራበት ወደ ተናገርኸው ወደዚህ ቤተ መቅደስ ዐይኖችህ ሌትና ቀን የተከፈቱ ይሁኑ ባሪያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውንም ጸሎት ስማ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ‘ስሜ ይጠራበታል’ ወዳልከው ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቀንና ሌሊት ተመልከት፤ እኔም አገልጋይህ ወደዚህ ቤተ መቅደስ የምጸልየውን ጸሎት ስማ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ባሪ​ያህ በዚህ ቤት የሚ​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦ በዚያ ስሜ ይሆ​ናል ወዳ​ል​ኸው ስፍራ፥ ወደ​ዚህ ቤት ዐይ​ኖ​ችህ ቀንና ሌሊት የተ​ገ​ለጡ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ባሪያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ‘በዚያ ስሜ ይሆናል፤’ ወዳልኸው ስፍራ፥ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ቀንና ሌሊት የተገለጡ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 6:20
17 Referencias Cruzadas  

ጌታ ጠባቂህ ነው፥ ጌታ በቀኝ እጅህ በኩል ይጋርድሃል።


ከክፉ ነገር ሽሽ መልካምንም አድርግ፥ ሰላምን እሻ ተከተላትም።


በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል ተገልጦ ይኖራልና፤


እኔ አገልጋይህ ዛሬ በፊትህ ስለ አገልጋዮችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ለመስማት ጆሮህ ያድምጥ፥ ዐይኖችህም ይከፈቱ፥ በአንተ ላይ ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኃጢአት እናዘዛለሁ፤ እኔና የአባቴ ቤት ኃጢአት አድርገናል።


ጌታ ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ለማጽናት ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። እንግዲህ አሁን የሞኞችን ተግባር ፈጽመሃል። ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይደረግብሃል።”


ነገር ግን ስሜ በዚያ እንዲጠራባት ኢየሩሳሌምን መርጫለሁ፥ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ እንዲሆን ዳዊትን መርጫለሁ።’


አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ የደረሰብንን ነገር ሁሉ ተመልከት፥ ሕያው አምላክን አንተን በመስደብ ሰናክሬም የተናገረውን የዛቻ ቃል ሁሉ አድምጥ፤


ጌታ እግዚአብሔር ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ሰብል በኲራቱን ሁሉ ውሰድ፤ በቅርጫትም ውስጥ አድርገው፤ ከዚያም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ጌታ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ።


ጌታ አምላካችሁም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፥ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፥ አሥራቶቻችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፥ እንዲሁም ለጌታ የተሳላችሁትን ምርጥ ነገሮች ሁሉ ወደዚያ ታመጣላችሁ።


ነገር ግን፥ አቤቱ አምላኬ ሆይ! ወደ ባርያህ ጸሎትና ልመና ተመልከት፥ ባርያህም በፊትህ የሚጸልየውን ጸሎትና ጥሪውን ስማ።


አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዐይኖቼ ይገለጣሉ፥ ጆሮቼም ያደምጣሉ።


‘ክፉ ነገር፥ ሰይፍ ወይም ፍርድ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን ስምህ ባለበት በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ ቆመን በመከራችን ወደ አንተ እንጮሃለን፥ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ።’


እነሆ፥ የጌታ ዐይኖች ወደሚፈሩት ናቸው፥ በቸርነቱም ወደሚታመኑ፥


‘ህዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ ስሜ የሚጠራበት ቤት በዚያ እንዲሠራልኝ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ማንኛውንም ከተማ አልመረጥሁም፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ አለቃ እንዲሆን ማንንም አልመረጥሁም፤


“አሁንም፥ አምላኬ ሆይ! በዚህ ስፍራ ወደሚሆነው ጸሎት ዐይኖችህ የተገለጡ፥ ጆሮችህም የሚያደምጡ እንዲሆኑ እባክህ እለምንሃለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios