እንዲሁም አንዱንም ኩሬ፥ በበታቹም የሚሆኑትን ዐሥራ ሁለት በሬዎች አበጀ።
ገንዳውና ከሥሩ ያሉትን ዐሥራ ሁለት ኰርማዎች፤
አንድዋንም ኵሬ፥ በበታችዋም ያሉትን ዐሥራ ሁለት በሬዎች ሠራ።
አንዱንም ኵሬ፥ በበታቹም የሚሆኑትን ዐሥራ ሁለት በሬዎች ሠራ።
መቀመጫዎቹንና በመቀመጫዎቹ ላይ የሚቀመጡትን የመታጠቢያ ሳሕኖች ሠራ፤
ምንቸቶቹንም መጫሪያዎቹንም ሜንጦዎቹንም ዕቃቸውንም ሁሉ ኪራም-አቢ ለንጉሡ ለሰሎሞን ለጌታ ቤት ከተሰነገለ ናስ ሠራ።