ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እኔ እግዚአብሔር በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ የማመጣው በጣም ከባድ መቅሠፍት ይህ ነው፤ ስለ እርሱም የሚሰማ ሰው ሁሉ በድንጋጤ ጭው ይላል፤
2 ዜና መዋዕል 34:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በይሁዳ ንጉሥ ፊት በተነበበው መጽሐፍ የተጻፉትን ቃላት ሁሉ፥ ማለት ክፉ ነገርን፥ በዚህ ስፍራና በነዋሪዎችዋ ላይ አመጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በይሁዳ ንጉሥ ፊት በተነበበው መጽሐፍ በተጻፈው ርግማን ሁሉ መሠረት፣ በዚህ ስፍራና በነዋሪዎቹ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃሉም እንዲህ የሚል ነበር፦ “እኔ እግዚአብሔር ለይሁዳ ንጉሥ በተነበበለት መጽሐፍ ውስጥ በሚገኙት እርግማኖች ኢየሩሳሌምንና ሕዝብዋን ሁሉ እቀጣለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ በይሁዳ ንጉሥ ፊት በተነበበው መጽሐፍ የተጻፉትን ቃላት ሁሉ፥ ማለት ክፉ ነገርን አመጣለሁ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ‘እነሆ፥ በይሁዳ ንጉሥ ፊት በተነበበው መጽሐፍ የተጻፉትን ቃላት ሁሉ፥ ማለት ክፉ ነገርን፥ በዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ አመጣለሁ። |
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እኔ እግዚአብሔር በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ የማመጣው በጣም ከባድ መቅሠፍት ይህ ነው፤ ስለ እርሱም የሚሰማ ሰው ሁሉ በድንጋጤ ጭው ይላል፤
ከአባቶቻችን ዘመን ጀምረን እስከ ዛሬ ድረስ በታላቅ በደል ነበርን፤ ዛሬም እንደ ሆነው ስለ ኃጢአታችን እኛ፥ ነገሥታቶችንና ካህናቶቻችን ለሰይፍ፥ ለምርኮ፥ ለብዝበዛና ለእፍረት በምድር ነገሥታት እጅ ተሰጠን።
“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና እነሆ፥ በዚህች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ።”
እንዲህም በል፦ ‘የይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ክፉን ነገር በዚህ ስፍራ ማምጣቴን የሚሰማ ጆሮ ሁሉ ጭው ይልበታል።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሆነ የሠራዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በተናገርኋቸው ጊዜ አልሰሙምና፥ በጠራኋቸውም ጊዜ አልመለሱልኝምና በእነርሱ ላይ የተናገርኩትን ክፉ ነገር ሁሉ በይሁዳ ላይ በኢየሩሳሌምም በተቀመጡ ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ።”
ስለ ኃጢአታቸውም እርሱንና ዘሩን ባርያዎቹንም እቀጣለሁ፤ እነርሱም አልሰሙምና በእነርሱ ላይ የተናገርሁትን ክፉ ነገር ሁሉ በእነርሱና በኢየሩሳሌም በተቀመጡ፥ በይሁዳም ሰዎች ላይ አመጣለሁ።’ ”
አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤልን ቤት፦ እናንተ፦ በደላችንና ኃጢአታችን በላያችን አሉ በእነርሱም እየመነመንን ነው፤ እንዴትስ በሕይወት እንኖራለን? ብላችሁ ተናግራችኋል በላቸው።
ጌታ አምላካችሁ ያዘዛችሁን ቃል ኪዳን ስታፈርሱ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ስታመልኩ፥ ስትሰግዱላቸውም፥ በዚያ ጊዜ የጌታ ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ከሰጣችሁም ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።”