2 ዜና መዋዕል 33:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ጸሎቱ፥ ጌታም እንደ ተለመነው፥ ኃጢአቱና መተላለፉ ሁሉ፥ ራሱንም ሳያዋርድ የኮረብታው መስገጃዎችን የሠራበት የማምለኪያ ዐፀዱንና የተቀረጹትንም ምስሎች የተከለበት ስፍራ፥ እነሆ፥ በባለ ራእዮቹ ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጸሎቱና እግዚአብሔር ራርቶ ልመናውን እንዴት እንደ ተቀበለው፣ ኀጢአቱ ሁሉና ታማኝነቱን ማጕደሉ፣ እንደዚሁም ራሱን ከማዋረዱ በፊት ያሠራቸው የኰረብታ መስገጃ ስፍራዎች፣ ያቆማቸው የአሼራ ምስል ዐምዶችና ጣዖታት ሁሉ በባለራእዮች መዛግብት ተጽፈዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ምናሴ ወደ እግዚአብሔር ያቀረበው ጸሎትና፥ እግዚአብሔርም ለጸሎቱ የሰጠው መልስ፥ ተጸጽቶ ንስሓ ከመግባቱ በፊት ያደረገው ኃጢአት ሁሉ፥ ማለትም የፈጸመው ልዩ ልዩ ክፋት፥ እርሱ ራሱ የሠራቸው የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችና አሼራ ተብላ የምትጠራው ሴት አምላክ ምስሎች፥ ያመልካቸው የነበሩ ጣዖቶች ሁሉ፥ በነቢያት የታሪክ መጻሕፍት ውስጥ ተመዝግበው ይገኛሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም አቤቱ፥ የጻድቃን አምላካቸው አንተ ነህ። ንስሓን የፈጠርህ ለጻድቅ ሰው አይደለምና፥ አንተን ላልበደሉ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም አይደለምና፤ ነገር ግን የእኔን የኃጥኡን ንስሓ ወደ ማየት ተመለስ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ጸሎቱ፥ እግዚአብሔርም እንደ ተለመነው፥ ኃጢያቱና መተላለፉ ሁሉ፥ ራሱንም ሳያዋርድ የኮረብታው መስገጃዎችን የሰራበት የማምለኪያ ዐፀዱንና የተቀረጹትንም ምስሎች የተከለበት ስፍራ፥ እነሆ፥ በባለ ራእዩ ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል። |
ስጦታውም አንድ ሰው ኃጢአትን በማድረጉ እንዳመጣው ውጤት አይደለም፤ በአንድ በኩል፥ ፍርዱ የአንድን ሰው በደል ተከትሎ ኩነኔን አመጣ፤ በሌላ በኩል ግን ስጦታው ብዙ በደልን ተከትሎ ጽድቅን አመጣ።