ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱን በውስጥ በኩል በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ እርሱም በወርቅ በተለበጠው ውስጠኛ ክፍል መግቢያ በር ክፈፉንም በተሸጋገሩ የወርቅ ሰንሰለቶች አስጌጠው።
2 ዜና መዋዕል 3:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ድሪ ያሉ ሰንሰለቶችንም ሠርቶ በዓምዶቹ ራስ ላይ አኖራቸው፤ መቶም ሮማኖች ሠርቶ በሰንሰለቱ ላይ አደረጋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርስ በርሳቸው የተጠላለፉ ሰንሰለቶች ሠርቶ ከዐምዶቹ ጫፍ ጋራ አገናኛቸው፤ ከዚያም መቶ የሮማን ፍሬዎች ሠርቶ ከሰንሰለቶቹ ጋራ አያያዛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምሰሶዎቹም ጫፎች የመርበብ ቅርጽ ባላቸው ሰንሰለቶችና ከነሐስ በተሠሩ ቊጥራቸው አንድ መቶ በሆነ የሮማን ፍሬ አምሳል የተሠራ ቅርጽ ተስሎባቸው ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ድሪ ያሉ ሰንሰለቶችንም ሠርቶ በአዕማዱ ራስ ላይ አደረጋቸው፤ መቶም ሮማኖች ሠርቶ በሰንሰለቱ ላይ አደረጋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ድሪ ያሉ ሰንሰለቶችንም ሠርቶ በዓምዶቹ ራስ ላይ አደረጋቸው፤ መቶም ሮማኖች ሠርቶ በሰንሰለቱ ላይ አደረጋቸው። |
ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱን በውስጥ በኩል በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ እርሱም በወርቅ በተለበጠው ውስጠኛ ክፍል መግቢያ በር ክፈፉንም በተሸጋገሩ የወርቅ ሰንሰለቶች አስጌጠው።
እነርሱም ከመረቡ በላይ ባለው ክብ ስፍራ እንዲቆሙ ተደረገ፤ በእያንዳንዱም ጉልላት ዙሪያ በሁለት ረድፍ የተደረደሩ ሁለት መቶ የሮማን ቅርጾች ነበሩ።
ዓምዶቹንም አንደኛውን በቀኝ፥ ሁለተኛውን በግራ በመቅደሱ ፊት አቆማቸው፥ በቀኝም የነበረውን ስም ያኪን በግራም የነበረውን ስም ቦዔዝ ብሎ ጠራቸው።
ሁለቱን ዓምዶች፥ ጽዋዎቹንም፥ በዓምዶቹም ላይ የነበሩትን ሁለት ጉልላቶች፥ በዓምዶቹም ላይ የነበሩትን የጉልላቶች ሁለቱን ጽዋዎች የሚሸፍኑትን ሁለቱን መርበቦች ሠራ።
በዓምዶቹም ላይ የነበሩትን ሁለቱን ጉልላቶች እንዲሸፍኑ፥ ለእያንዳንዱ መረበብ በሁለት በሁለት ረድፍ ያሉ ሮማኖች፥ ለሁለቱ መርበቦች አራት መቶ ሮማኖች አደረገ።