የአሮንን ልጆች የጌታን ካህናትና ሌዋውያንን አላሳደዳችሁምን? እንደ ሌሎችም አሕዛብ ልማድ ለራሳችሁ ካህናትን አልሾማችሁምን? አንድ ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ይዞ ለመቀደስ የሚመጣ ሁሉ አማልክት ላልሆኑት ለእነዚያ ካህን ይሆናል።
2 ዜና መዋዕል 29:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቅያስም፦ “አሁን ለጌታ ተቀድሳችኋል፤ ቅረቡ፥ መሥዋዕቱንና የምስጋናውን መሥዋዕት ወደ ጌታ ቤት አምጡ” ብሎ ተናገረ። ጉባኤውም መሥዋዕቱንና የምስጋናውን መሥዋዕት አመጡ፤ ልባቸውም የፈቀደ ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሕዝቅያስ፣ “እነሆ፤ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሳችኋል፤ አሁንም ቅረቡ፤ መሥዋዕትና የምስጋና ስጦታ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አምጡ” አላቸው። ስለዚህ ጉባኤው መሥዋዕትና የምስጋና ስጦታ አመጡ፤ ልባቸው የፈቀደ ሁሉም የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሕዝቅያስም ሕዝቡን “አሁን ራሳችሁን ለእግዚአብሔር የለያችሁ ስለ ሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ለማቅረብ መሥዋዕታችሁን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አምጡ!” አላቸው፤ እነርሱም ንጉሡ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ አንዳዶቹም በገዛ ፈቃዳቸው ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶችን አመጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቅያስም፥ “አሁን እጃችሁን ለእግዚአብሔር አንጽታችሁ ቅረቡ፤ መሥዋዕቱንና የምስጋናውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጡ” ብሎ ተናገረ። ጉባኤውም መሥዋዕቱንና የምስጋናውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጡ፤ ልባቸውም የፈቀደ ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቅያስም “አሁን ለእግዚአብሔር ተቀድሳችኋል፤ ቅረቡ፤ መሥዋዕቱንና የምስጋናውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጡ፤” ብሎ ተናገረ። ጉባኤውም መሥዋዕቱንና የምስጋናውን መሥዋዕት አመጡ፤ ልባቸውም የፈቀደ ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አመጡ። |
የአሮንን ልጆች የጌታን ካህናትና ሌዋውያንን አላሳደዳችሁምን? እንደ ሌሎችም አሕዛብ ልማድ ለራሳችሁ ካህናትን አልሾማችሁምን? አንድ ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ይዞ ለመቀደስ የሚመጣ ሁሉ አማልክት ላልሆኑት ለእነዚያ ካህን ይሆናል።
ጉባኤውም ያመጡት የሚቃጠል መሥዋዕት ቍጥር ሰባ በሬዎች፥ መቶም አውራ በጎች፥ ሁለት መቶም የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ ይህ ሁሉ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ።
ከሁሉም ስፍራዎች የተረፈው ሁሉ መፃተኛ ሆኖ በሚኖርበት የሰፈሩ ሰዎች በብርና በወርቅ በዕቃም በእንስሳም ይርዱት፥ ይህም በኢየሩሳሌም ላለው ለእግዚአብሔር ቤት በፈቃዳቸው ከሚያቀርቡት መባ ጋር ይሁን።”
ልባቸው የተነሣሣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ የአፍንጫ ጌጦችን፥ ሎቲዎችን፥ ቀለበቶችን፥ ድሪዎችን፥ የወርቅ ጌጦችን ሁሉ አመጡ፤ ሰዎች ሁሉ የወርቅ ስጦታ ለጌታ አመጡ።
መስፍኑ በፈቃዱ የሚያቀርበውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ወይም የሰላሙን መሥዋዕት፥ በፈቃዱ ለጌታ የሚያቀርበውን መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ፥ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ይከፈትለት፥ በሰንበትም ቀን እንደሚያደርግ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሰላሙን መሥዋዕት ያቅርብ፤ ከዚያ በኋላ ይውጣ፥ ከወጣም በኋላ በሩ ይዘጋ።
እነዚህም ከጌታ ሰንበታት ሌላ፥ ለጌታም ከምትሰጡት ከስጦታችሁ ሌላ፥ ከስእለታችሁም ሁሉ ሌላ፥ በፈቃዳችሁም ከምታቀርቡአቸው ሁሉ ሌላ ናቸው።
የሚያቀርውም ለምስጋና ቢሆን፥ ከምስጋናው መሥዋዕት ጋር እርሾ ያልገባበት በዘይት የተለወሰ የቂጣ እንጎቻ፥ እርሾ ያልነካው በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ፥ በዘይትም የተለወሰ መልካም ዱቄት ያቀርባል።