La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 26:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ታላቁም ካህን ዓዛርያስ ካህናቱም ሁሉ ተመለከቱት፥ እነሆም፥ በግምባሩ ላይ ለምጽ ነበረ፤ ፈጥነውም እንዲወጣ አስገደዱት፥ እርሱም ደግሞ ጌታ ቀሥፎት ነበርና ለመውጣት ቸኮለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሊቀ ካህናቱ ዓዛርያስና ሌሎቹ ካህናት ሁሉ በተመለከቱት ጊዜ፣ በግንባሩ ላይ ለምጽ እንደ ወጣበት አዩ። ስለዚህ አጣድፈው አስወጡት፤ በርግጥ እርሱም ራሱ ለመውጣት ቸኵሎ ነበር፤ እግዚአብሔር አስጨንቆታልና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዐዛርያስና ሌሎቹም ካህናት በታላቅ ድንጋጤ የንጉሡን ግንባር ትኲር ብለው ተመለከቱ፤ ከቤተ መቅደስም እንዲወጣ አስገደዱት፤ ዖዝያም እግዚአብሔር እንደ ቀጣው ዐውቆ ለመውጣት ተጣደፈ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ታላቁ ካህን ዓዛ​ር​ያስ፥ ካህ​ና​ቱም ሁሉ ተመ​ለ​ከ​ቱት፤ እነ​ሆም፥ በግ​ን​ባሩ ላይ ለምጽ ነበረ፤ ፈጥ​ነ​ውም አባ​ረ​ሩት፤ እር​ሱም ደግሞ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር ቀሥ​ፎት ነበ​ርና ይወጣ ዘንድ ቸኰለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ታላቁም ካህን ዓዛርያስ ካህናቱም ሁሉ ተመለከቱት፤ እነሆም፥ በግምባሩ ላይ ለምጽ ነበረ፤ ፈጥነውም አባርረሩት፤ እርሱም ደግሞ እግዚአብሔር ቀሥፎት ነበርና ይወጣ ዘንድ ቸኮለ።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 26:20
8 Referencias Cruzadas  

ዖዝያንም ተቈጣ፤ የሚያጥንበትም ጥና በእጁ ነበረ፤ ካህናቱንም በተቈጣ ጊዜ በካህናቱ ፊት በጌታ ቤት ውስጥ በዕጣኑ መሠዊያ አጠገብ ሳለ በግምባሩ ላይ ለምጽ ታየ።


ንጉሡም ዖዝያን እስኪሞት ድረስ ለምጻም ነበረ፤ ለምጻምም ሆኖ ከጌታ ቤት ተነጥሎአልና በተለየ ቤት ይቀመጥ ነበር፤ ልጁም ኢዮአታም በንጉሡ ቤት ላይ ሆኖ በምድሩ ሕዝብ ላይ ይፈርድ ነበር።


የአቢሹዓ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የኤልዓዛር ልጅ፥ የታላቁ ካህን የአሮን ልጅ፥


ካህኑም ያያል፤ እነሆም፥ በቆዳው ላይ ነጭ እባጭ ቢኖር፥ በእርሱም ላይ ያለውን ጠጉር ለውጦት ቢያነጣው፥ ሥጋውም በእባጩ ውስጥ ቢያዥ፥


“እኔ ወደምሰጣችሁ ርስት ወደ ከነዓን ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ በምትወርሱአት ምድር በአንድ ቤት ውስጥ የለምጽ ደዌ ባኖር፥


ጌታ እስክትጠፋ ድረስ በሚቀሥፍ በሽታ ንዳድና ዕባጭ፥ ኀይለኛ ሙቀትና ድርቅ፥ ዋግና አረማሞ ይመታሃል።


ጌታ ከእግርህ ጥፍር እስከ ራስህ ጠጉር በሚዛመት፥ ሊድን በማይችልና በሚያሠቃይ ቁስል ጉልበትህንና እግርህን ይመታሃል።