ይህም የሆነበት ምክንያት ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ጌታ የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ንጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን ሐሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት ጌታ ይህን ለውጥ ለማድረግ ስለ ወሰነ ነው።
2 ዜና መዋዕል 22:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አካዝያስም ወደ ኢዮራም በመምጣቱ እዲጠፋ የጌታ ፈቃድ ነበረ፤ በመጣም ጊዜ ከኢዮራም ጋር ጌታ የአክዓብን ቤት እንዲያጠፋ ወደ ቀባው ወደ ናሜሲ ልጅ ወደ ኢዩ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አካዝያስ ኢዮራምን ለመጠየቅ መሄዱን፣ እግዚአብሔር ለአካዝያስ መውደቅ ምክንያት አደረገው፤ አካዝያስ እንደ ደረሰም የናሜሲን ልጅ ኢዩን ለመቀበል ከኢዮራም ጋራ ወጣ፤ ኢዩም የአክዓብን ቤት እንዲያጠፋ እግዚአብሔር የቀባው ሰው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አካዝያስ ኢዮራምን ሊጠይቅ የሄደው እግዚአብሔር ይህ ጒብኝት የአካዝያስ መጥፊያ እንዲሆን ስለ ፈቀደ ነው፤ አካዝያስ በዚያ በነበረበት ጊዜ እርሱና ኢዮራም የአክዓብን ሥርወ መንግሥት ለማጥፋት እግዚአብሔር የመረጠውን የኒምሺ ልጅ ኢዩን ለመቀበል ወጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ኢዮራም በመምጣቱም የአካዝያስ ጥፋት ከእግዚአብሔር ሆነ፤ በመጣም ጊዜ ከኢዮራም ጋር እግዚአብሔር የአክዓብን ቤት ያጠፋ ዘንድ ወደ ቀባው ወደ ናሚሲ ልጅ ወደ ኢዩ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አካዝያስም ወደ ኢዮራም በመምጣቱ ይጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበረ፤ በመጣም ጊዜ ከኢዮራም ጋር እግዚአብሔር የአክዓብን ቤት ያጠፋ ዘንድ ወደ ቀባው ወደ ናሜሲ ልጅ ወደ ኢዩ ወጣ። |
ይህም የሆነበት ምክንያት ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ጌታ የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ንጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን ሐሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት ጌታ ይህን ለውጥ ለማድረግ ስለ ወሰነ ነው።
“ወንድሞቻችሁ በሆኑት በእስራኤላውያን ላይ አደጋ አትጣሉ፤ ሁላችሁም ወደየቤታችሁ ሂዱ፤ ይህ የሆነውም በእኔ ፈቃድ ነው” ብሎ እንዲነግር አዘዘው። እነርሱም ሁሉ ለጌታ ቃል ታዛዦች በመሆን ወደየቤታቸው ተመልሰው ሄዱ።
የኒምሺን ልጅ ኢዩንም ቀብተህ በእስራኤል ላይ አንግሠው፤ የአቤል መሖላ ተወላጅ የሆነውን የዮሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕንም ቀብተህ በአንተ እግር ነቢይ እንዲሆን አድርገው።
ጌታም ‘አክዓብ ወደ ራሞት ሄዶ በዚያ እንዲገደል ሊያሳስተው የሚችል ማነው?’ አለ፤ ከመላእክቱም መካከል አንዱ አንድ ነገር፥ ሌላው ሌላ ነገር በመግለጥ የተለያየ ሐሳብ ያቀርቡ ነበር።
ከዚህም በኋላ ኢዩ በኢይዝራኤል የሚኖሩትን ሌሎቹን የአክዓብን ዘመዶች፥ ባለሟሎቹ የነበሩትን ባለ ሥልጣኖች እንዲሁም የቅርብ ወዳጆቹንና ካህናቱን አንድም ሳይቀር ሁሉንም ገደለ።
ከዚህ በኋላ ንጉሥ ኢዮራም “ሠረገላዬን አዘጋጅልኝ” ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ ሠረገላውም ተዘጋጅቶለት እርሱና ንጉሥ አካዝያስ በየግል ሠረገላቸው እየጋለቡ ኢዩን ሊገናኙት ወጡ፤ እነርሱም ኢዩን ቀድሞ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ አገኙት።
ንጉሥ አካዝያስ የሆነውን ነገር ሁሉ በተመለከተ ጊዜ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ወደ ቤትሀጋን ከተማ ሸሽቶ ሄደ፤ ኢዩ ተከታትሎ እያሳደደው “እርሱንም ግደሉት!” ሲል ለወታደሮቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም አካዝያስን ተከታትለው በዪብለዓም ከተማ አጠገብ በምትገኘው በጉር የአቀበት መንገድ ላይ በሠረገላው ሲበር መትተው አቆሰሉት፤ እርሱ ግን እንደ ምንም ጨክኖ መጊዶ ከተማ እስኪደርስ ተጓዘ፤ በዚያም ሞተ፤
ጌታም በሴሎናዊው በአሒያ አድርጎ ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረውን ቃል እንዲያጸና ከጌታ ዘንድ ተወስኖ ነበርና ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም።
ከሶርያም ንጉሥ ከአዛኤል ጋር በተዋጋ ጊዜ ሶርያውያን በሬማት ያቈሰሉትን ቁስል ለመታከም ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ፤ ታምሞም ነበርና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የአክዓብን ልጅ ኢዮራምን ለማየት ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።
ኤፍሬም ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ከጣዖታት ጋር እኔ ምን አደርጋለሁ? እኔ እመልስለታለሁ፥ ወደ እርሱም እመለከታለሁ፤ እኔ እንደ ለመለመ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህ በእኔ ዘንድ ይገኛል።
ጌታ ሙሴን እንዳዘዘ፥ እንዲያጠፉአቸው ምሕረትንም ሳያደርጉ ፈጽመው እንዲፈጅዋቸው፥ ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ልባቸውን እንዲያደነድኑ ከጌታ ዘንድ ሆነ።
በዚያን ጊዜ በእስራኤል ላይ ገዦቹ ፍልስጥኤማውያን ስለ ነበሩ፥ ከፍልስጥአማውያን ጋር ጠብ እንዲፈጠር ጌታ ሆን ብሎ ያደረገው ነገር መሆኑን አባቱና እናቱ አላወቁም ነበር።