የንጉሡ ልጅ ዮሳቤት ግን ከተገደሉት ከንጉሡ ልጆች መካከል የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ሰርቃ ወሰደች፤ እርሱንና ሞግዚቱን በእልፍኝ ውስጥ አኖረቻቸው፤ ጎቶሊያ እንዳታስገድለው የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የአካዝያስ እኅት የካህኑ የዮዳሄ ሚስት ዮሳቤት እንዲሁ ሸሸገችው።
2 ዜና መዋዕል 22:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእነርሱም ዘንድ ተሸሽጎ በጌታ ቤት ስድስት ዓመት ያህል ተቀመጠ፤ ጎቶልያም በምድሪቱ ላይ ነገሠች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ጎቶልያ ምድሪቱን በምትገዛበት ጊዜ ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተደብቆ ስድስት ዓመት ዐብሯቸው ኖረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዐታልያ ዘመነ መንግሥት ኢዮአስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ስድስት ዓመት ሙሉ ተደብቆ ኖረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርስዋም ጋር በእግዚአብሔር ቤት ተሸሽጎ ስድስት ዓመት ያህል ተቀመጠ፤ ጎቶልያም በምድር ላይ ነገሠች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእነርሱም ዘንድ ተሸሽጎ በእግዚአብሔር ቤት ስድስት ዓመት ያህል ተቀመጠ፤ ጎቶልያም በምድር ላይ ነገሠች። |
የንጉሡ ልጅ ዮሳቤት ግን ከተገደሉት ከንጉሡ ልጆች መካከል የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ሰርቃ ወሰደች፤ እርሱንና ሞግዚቱን በእልፍኝ ውስጥ አኖረቻቸው፤ ጎቶሊያ እንዳታስገድለው የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የአካዝያስ እኅት የካህኑ የዮዳሄ ሚስት ዮሳቤት እንዲሁ ሸሸገችው።
በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ በረታ፥ የመቶ አለቆቹንም፥ የይሮሐምን ልጅ ዓዛርያስን፥ የይሆሐናንንም ልጅ ይስማኤልን፥ የዖቤድንም ልጅ ዓዛሪያስን፥ የዓዳያንም ልጅ መዕሤያን፥ የዝክሪንም ልጅ ኤሊሳፋጥን ወስዶ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።
አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚበድሉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል?
ጌታ አምላኬ፥ ቅዱሴ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፤ ጌታ ሆይ፥ ለፍርድ ወስነሃቸዋል፥ ዓለት ሆይ ለተግሣጽም መሠረትሃቸው።