እርሷም፥ “ደም ተበቃዮቹ ተጨማሪ ደም እንዳያፈሱ ልጄም እንዳይገደል፥ ንጉሡ ጌታ አምላኩን ያስብ” አለች። ንጉሡም፥ “ሕያው በሆነው ጌታ እምላለሁ! ከልጅሽ አንድ ጠጉር በምድር ላይ አይወድቅም” አላት።
2 ዜና መዋዕል 20:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላካችን ሆይ! አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን ልንቋቋመው አንችልም፤ ዐይኖቻችን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር የምናደርገውን ነገር አናውቅም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችን ሆይ፤ አንተ አትፈርድባቸውምን? የመጣብንን ይህን ታላቅ ሰራዊት እንቋቋም ዘንድ ዐቅም የለንምና የምናደርገውን አናውቅም፤ ነገር ግን ዐይኖቻችን ወዳንተ ናቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላካችን ሆይ! በእኛ ላይ አደጋ ሊጥሉ በብዛት የመጡትን እነዚህን ሠራዊት ሁሉ መቋቋም ስለማንችል አንተ ራስህ ፍረድባቸው፤ የአንተን ርዳታ ለማግኘት ዐይናችንን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር ሌላ ምንም ማድረግ እንደሚገባን አናውቅም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችን ሆይ፥ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን መቃወም እንችል ዘንድ ኀይል የለንም፤ የምናደርግባቸውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዐይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችን ሆይ! አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን እንቃወም ዘንድ አንችልም፤ የምናደርገውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዓይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው።” |
እርሷም፥ “ደም ተበቃዮቹ ተጨማሪ ደም እንዳያፈሱ ልጄም እንዳይገደል፥ ንጉሡ ጌታ አምላኩን ያስብ” አለች። ንጉሡም፥ “ሕያው በሆነው ጌታ እምላለሁ! ከልጅሽ አንድ ጠጉር በምድር ላይ አይወድቅም” አላት።
በማግስቱም ማለዳ የኤልሳዕ አገልጋይ ከመኝታው ተነሥቶ፥ ከቤት ሲወጣ በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀቡ የሶርያ ወታደሮች ከተማይቱን መክበባቸውን አየ፤ ወደ ኤልሳዕም ተመልሶ ድምፁን ከፍ በማድረግ “ጌታዬ ወዮ! ምን ማድረግ ይሻለናል?” ሲል ጠየቀው።
እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል። እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ። ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም።
እኔ አልበደልሁህም፤ አንተ ግን በእኔ ላይ ዘምተህ በድለኸኛል፤ እንግዲህማ ፈራጅ የሆነው ጌታ በእስራኤላውያንና በአሞናውያን መካከል ዛሬ ይፍረድ።”
ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፤ ወደነዚያ ያልተገረዙ ሰዎች ጦር ሰፈር እንሻገር፤ ምናልባትም ጌታ ይዋጋልን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት ለማዳን ጌታን የሚያግደው የለምና” አለው።
ልጆቹ አስጸያፊ ነገር ሲያደርጉ እርሱ ባለመከልከሉ፥ ዔሊ በሚያውቀው ኃጢአት ምክንያት በቤተሰቡ ላይ ለዘለዓለም እንደምፈርድ ነግሬው ነበር።