Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 7:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የአሕዛብም ጉባኤ ይከብብሃል፥ በእነርሱም ላይ ወደ ከፍታ ተመለስ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል። እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ጽድቄ ፍረድልኝ፤ ልዑል ሆይ፤ እንደ ቅን አካሄዴ መልስልኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል፤ ጌታ ሆይ! እንደ እውነተኛነቴና እንደ ታማኝነቴ ፍረድልኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝብ ላይ ይፈ​ር​ዳል፤ አቤቱ አም​ላኬ፥ እንደ ጽድ​ቅህ ፍረ​ድ​ልኝ፤ እንደ የዋ​ህ​ነ​ቴም ይሁ​ን​ልኝ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 7:8
23 Referencias Cruzadas  

ይመጣልና፥ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፥ እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።


አቤቱ፥ ፍረድልኝ፥ ከጽድቅ በራቁም ሕዝብ ዘንድ ተሟገትልኝ፥ ከሸንጋይና ከግፈኛ ሰው አድነኝ።


ዓለምንም በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።


በእናንተ በአማኞች መካከል እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ኑሮ እንደ ነበርን እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤


ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።


በልቡ ቅንነት ጠበቃቸው፥ በእጁም ብልሃት መራቸው።


የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ እኔ በቅንነት ሄጃለሁና ፍረድልኝ፥ በጌታም አምኛለሁና አልናወጥም።


ጠላቴ እልል አይልብኝምና በዚህም በእኔ እንደ ተደሰትክ አወቅሁ።


እኔ ግን በቅንነት ሄጃለሁ፥ አድነኝ ማረኝም።


አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና ፍጽምናና ቅንነት ይጠብቁኝ።


ጌታ በተቀደሰው መቅደሱ ነው፥ ጌታ፥ ዙፋኑ በሰማይ ነው፥ ዐይኖቹ ይመለከታሉ፥ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።


ጌታ ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥ ዙፋኑንም ለመፍረድ አዘጋጀ፥


አምላካችን ሆይ! አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን ልንቋቋመው አንችልም፤ ዐይኖቻችን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር የምናደርገውን ነገር አናውቅም።”


የአብርሃም አምላክ የናኮርም አምላክ፥ የአባታቸውም አምላክ፥ በእኛ መካከል ይፍረድ።” ያዕቆብም በአባቱ በይስሐቅ ፍርሃት ማለ።


ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?”


ቀንቀጥሮአልና፤ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።”


በከንፈሩ ከሚወሳልት ሰነፍ ይልቅ ያለ ነውር የሚሄድ ድሀ ይሻላል።


የአሳፍ መዝሙር። እግዚአብሔር በመለኮታዊ ጉባኤ ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios