ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል በፈቃደኝነት ልናቀርብልህ የምንችል እኔ ማን ነኝ? ሕዝቤስ ማን ነው?
2 ዜና መዋዕል 17:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም በኋላ በፈቃዱ ራሱን ለጌታ የቀደሰ የዝክሪ ልጅ ዓማስያ፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ ቀጥሎም ለእግዚአብሔር አገልግሎት በፈቃደኛነት ራሱን የሰጠው የዝክሪ ልጅ ዓማስያ ከሁለት መቶ ሺሕ ተዋጊዎች ጋራ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከይሆሐናን ቀጥሎ በማዕርግ ሦስተኛ የሆነው የጦር መኰንን የዚክሪ ልጅ ዐማሥያ ነበር፤ በእርሱም ሥር ሁለት መቶ ሺህ ወታደሮች ነበሩ፤ እርሱም በገዛ ፈቃዱ ራሱን ለእግዚአብሔር አገልግሎት የለየ የጦር አዛዥ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም በኋላ እግዚአብሔርን የሚያገለግል የዝክሪ ልጅ ማስያስ፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም በኋላ በፈቃዱ ራሱን ለእግዚአብሔር የቀደሰ የዝክሪ ልጅ ዓማስያ፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ። |
ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል በፈቃደኝነት ልናቀርብልህ የምንችል እኔ ማን ነኝ? ሕዝቤስ ማን ነው?
አምላኬ ሆይ! ልብን እንደምትመረምር፥ ቅንነትንም እንደምትወድድ አውቃለሁ፤ እኔም በልቤ ቅንነትና በፈቃዴ ይህን ሁሉ አቅርቤአለሁ፤ አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በፈቃዱና ደስ ተሰኝቶ እንዳቀረበልህ አይቻለሁ።