2 ዜና መዋዕል 13:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ከይሁዳ ፊት ሸሹ፥ ጌታም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ከይሁዳ ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያንም ከይሁዳ ሰዎች ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ለይሁዳ ሕዝብ አሳልፎ ሰጣቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ከይሁዳ ሰዎች ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ከይሁዳ ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። |
ኢትዮጵያውያንና የልብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረገሎችና ፈረሰኞች የነበሩአቸው እጅግ ታላቅ ሠራዊት አልነበሩምን? በጌታ ስለ ታመንህ በእጅህ አሳልፎ ሰጣቸው፥
በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ፥ የትኛይቱም ከተማ አልተቋቋመችንም፤ ጌታ አምላካችን ሁሉን አሳልፎ ሰጠን።
ስለዚህ ጌታ አምላካችን ደግሞ የባሳንን ንጉሥ ዖግን ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፥ እኛም አንድ ሰው እንኳ ሳናስቀርለት አጠፋነው።
ጌታም በእስራኤል ልጆች እጅ አሞራውያንን አሳልፎ በሰጠ ቀን ኢያሱ ለጌታ እንዲህ ብሎ ተናገረ፤ የእስራኤልም ልጆች እያዩ እንዲህ አለ፦ “በገባዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፥ በኤሎንም ሸለቆ ጨረቃ፤”
ጌታም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፤ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ማንም ሰው ሊቋቋማቸው አልቻለም፤ ጌታም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።
“ከዚያም የእስራኤል አምላክ ጌታ ሴዎንንና ሕዝቡን ሁሉ በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤” አሸነፏቸውም፤ እስራኤልም በዚያ አገር የሚኖሩትን የአሞራውያንን ምድር በሙሉ ወረሰ፤
ሳኦል የዳዊትን ወደ ቅዒላ መሄድ በሰማ ጊዜ፥ “ዳዊት መዝጊያና የብረት መወርወሪያ ወዳላት ከተማ መግባቱ፥ ራሱን በራሱ እንደ ማሰር ስለ ሆነ፥ ይህን ሰው እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ቢሰጠኝ ነው” አለ።