Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 13:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከይ​ሁዳ ሰዎች ፊት ሸሹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እስራኤላውያን ከይሁዳ ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የእስራኤልም ልጆች ከይሁዳ ፊት ሸሹ፥ ጌታም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እስራኤላውያንም ከይሁዳ ሰዎች ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ለይሁዳ ሕዝብ አሳልፎ ሰጣቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የእስራኤልም ልጆች ከይሁዳ ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 13:16
10 Referencias Cruzadas  

ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንና የል​ብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች የነ​በ​ሩ​አ​ቸው እጅግ ታላቅ ጭፍራ አል​ነ​በ​ሩ​ምን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ታመ​ንህ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


ለሳ​ኦ​ልም ዳዊት ወደ ቂአላ እንደ መጣ ተነ​ገ​ረው፤ ሳኦ​ልም፥ “መዝ​ጊ​ያና መወ​ር​ወ​ሪያ ወዳ​ለ​ባት ከተማ ገብቶ ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጄ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ታል” አለ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሴዎ​ን​ንና ሕዝ​ቡን ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጠ፤ ገደ​ሉ​አ​ቸ​ውም፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በዚያ ምድር ተቀ​ም​ጠው የነ​በ​ሩ​ትን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ምድር ሁሉ ወረሱ።


ይሁ​ዳም ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንና ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን በእጁ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በቤ​ዜቅ ውስጥ ዐሥር ሺህ ሰዎ​ችን ገደ​ለ​ባ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እንደ ማለ​ላ​ቸው በዙ​ሪ​ያ​ቸው ካሉት አሳ​ረ​ፋ​ቸው፤ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ይቋ​ቋ​ማ​ቸው ዘንድ ማንም ሰው አል​ቻ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


ያን ጊዜም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እጅ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አሳ​ልፎ ሰጠ፤ እርሱ በገ​ባ​ዖን እነ​ር​ሱን ባጠ​ፋ​በት፥ እነ​ር​ሱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት በጠ​ፉ​በት ቀን ኢያሱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ተነ​ጋ​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “በገ​ባ​ዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፤ በኢ​ሎ​ንም ሸለቆ ጨረቃ፤”


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ የባ​ሳ​ንን ንጉሥ ዐግን ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጠን፤ እኛም አጠ​ፋ​ነው፤ አንድ ሰው እን​ኳን ለዘር አል​ቀ​ረ​ለ​ትም።


በአ​ር​ኖን ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔ​ርና በሸ​ለ​ቆ​ውም ውስጥ ካለ​ችው ከተማ ጀም​ረን እስከ ገለ​ዓድ ተራራ ድረስ ማን​ኛ​ዪ​ቱም ከተማ አላ​መ​ለ​ጠ​ች​ንም፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ችን ሰጠን።


ጠላ​ቶ​ች​ህን በእ​ጅህ የጣ​ለ​ልህ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቡሩክ ነው” አለው። አብ​ራ​ምም ከሁሉ ዐሥ​ራ​ትን ሰጠው።


አብ​ያና ሕዝ​ቡም ታላቅ አመ​ታት መቱ​አ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ስት መቶ ሺህ የተ​መ​ረጡ ሰዎች ተገ​ድ​ለው ወደቁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios