1 ጢሞቴዎስ 5:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም ጎን ለጎን ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ ፈቶችም ብቻ ሳይሆኑ የማይገባቸውን እየተናገሩ ሰውን የሚያሙና በነገር ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተጨማሪም ሥራ መፍታትንና ከቤት ቤት መዞርን ይለምዳሉ፤ ሥራ ፈት መሆን ብቻ ሳይሆን፣ የማይገባውን እየተናገሩ ሐሜተኞችና በሰው ጕዳይም ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ መፍታት ብቻ ሳይሆን በየሰዉ ቤት እየዞሩ ሰውን የሚያሙ፥ በሰው ነገር የሚገቡና መናገር የማይገባቸውን የሚናገሩ ይሆናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም ጋር ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራን መፍታት ደግሞ ይማራሉ፤ የማይገባውንም እየተናገሩ ለፍላፊዎችና በነገር ገቢዎች ይሆናሉ እንጂ፥ ሥራ ፈቶች ብቻ አይደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም ጋር ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራን መፍታት ደግሞ ይማራሉ፥ የማይገባውንም እየተናገሩ ለፍላፊዎችና በነገር ገቢዎች ይሆናሉ እንጂ፥ ሥራ ፈቶች ብቻ አይደሉም። |
ማንም ከእናንተ መካከል እንደ ነፍሰ ገዳይ፥ ወይም እንደ ሌባ፥ ወይም እንደ ክፉ አድራጊ፥ ወይም በሌሎች ጉዳይ ጣልቃ እንደሚገባ ሆኖ መከራ የሚቀበል አይኑር።
ስለዚህ እኔ ከመጣሁ፥ ስለ እኛ የተናገረውን ክፉ ቃል፥ የሠራውን ሥራ አሳስበዋለሁ፤ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም፤ ሊቀበሉአቸው የሚፈልጉትን ይከለክላቸዋል፥ ከቤተ ክርስቲያንም ያስወጣቸዋል።