1 ተሰሎንቄ 5:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ሁላችሁም የብርሃን ልጆች፥ የቀንም ልጆች ናችሁና፤ ሆኖም እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁላችሁም የብርሃን ልጆች፣ የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ ወገን አይደለንም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ሁላችሁም የብርሃን ሰዎች፥ የቀንም ሰዎች ናችሁ፤ እኛ የሌሊት ወይም የጨለማ ሰዎች አይደለንም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና፤ እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም፤ |
በሌላ በኩል አዲስ ትእዛዝን እጽፍላችኋለሁ፥ ይህም በእርሱ እና በእናንተ ዘንድ እውነት ነው፤ ጨለማው አልፏል፥ እውነተኛው ብርሃን እያበራ ነው።