Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ተሰሎንቄ 5:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ወንድሞች ሆይ! እናንተ ግን ቀኑ እንደ ሌባ እንዳይመጣባችሁ በጨለማ ውስጥ አይደላችሁም፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እናንተ ግን፣ ወንድሞች ሆይ፤ ይህ ቀን እንደ ሌባ ያስደነግጣችሁ ዘንድ በጨለማ ውስጥ አይደላችሁም፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ፥ በጨለማ ውስጥ አይደላችሁም፤ ስለዚህ ቀኑ እንደ ሌባ አይመጣባችሁም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ! ቀኑ እንደ ሌባ ይደርስባችሁ ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እናንተ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ቀኑ እንደ ሌባ ይደርስባችሁ ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም፥

Ver Capítulo Copiar




1 ተሰሎንቄ 5:4
17 Referencias Cruzadas  

በሌላ በኩል አዲስ ትእዛዝን እጽፍላችኋለሁ፥ ይህም በእርሱ እና በእናንተ ዘንድ እውነት ነው፤ ጨለማው አልፏል፥ እውነተኛው ብርሃን እያበራ ነው።


የጌታ ቀን ግን እንደ ሌባ በድንገት ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ ምድርም በእርሷም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።


እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፤ ወደ ተወደደውም ልጁ መንግሥት አፈለሰን፤


ነገር ግን ለአገልጋዮቼ ለነቢያት ያዘዝኳቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? ከዚያ እነርሱም ተጸጽተው፦ “የሠራዊት ጌታ በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ሊያደርግብን ያሰበውን እንዲሁ አድርጎብናል” በማለት ተቀበሉ።


እስራኤል ሆይ! ከጊብዓ ዘመን ጀምረህ ኃጢአትን ሠርተሃል፤ በዚያ ጸንተዋል፤ በዓመፀኛ ልጆች ላይ በጊብዓ ጦርነት አይደርስባቸውምን?


የምትፈሩት ሰይፍ በዚያ በግብጽ ምድር ይደርስባችኋል፥ የሚያስደነግጣችሁም ራብ በዚያ በግብጽ ይከተላችኋል፥ በዚያም ትሞታላችሁ።


“ጌታ እግዚአብሔርን ስላልታዘዝህና የሰጠህን ትእዛዝና ሥርዓት ስላልጠበቅህ እነዚህ ርግማኖች ሁሉ በአንተ ላይ ይመጣሉ፥ እስክትጠፋ ድረስ ያሳድዱህማል፥ ይወርሱሃል።


“ነገር ግን ለጌታ ለእግዚአብሔር ባትታዘዝ በዛሬዋ ዕለት የምሰጥህን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ሁሉ በጥንቃቄ ባትከተላቸው፥ እነዚህ ርግማኖች ሁሉ ይደርሱብሃል፤ ያጥለቀልቁሃልም፦


አለበለዚያ በተንኰል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ቢገድል፥ መንገዱ ረጅም ከሆነ ደም ተበቃዩ በንዴት ተከታትሎ ይደርስበትና፥ መገደል የማይገባውን ሰው ሊገድል ይችላል።


እንግዲህ ቃሉን እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስታውስ፤ ጠብቀውም፤ ንስሓም ግባ። ባትነቃ ግን እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ፤ በማናቸውም ሰዓት እንደምመጣብህ ከቶ አታውቅም።


እውነት እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ አገር ይቀልላቸዋል።


“ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር፥ ስለ ኑሮም ማሰብ እንዳይዝል፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤


የጌታ ቀን ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ የሚመጣ መሆኑን እናንተው ራሳችሁ በጥንቃቄ አውቃችኋልና።


“እነሆ እንደ ሌባ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ ኀፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios